Connect with us

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች  የጋራ መግለጫ አወጡ

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ አወጡ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች  የጋራ መግለጫ አወጡ

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች  የጋራ መግለጫ አወጡ

 

የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጅግጅጋ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ስለ ሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች በመወያየት ባለ 4 ነጥብ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የጋራ መግለጫ ያወጡት ፓርቲዎች የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ዱቦና ድግኖ ፓርቲ፣ የምዕራብ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ የብልፅግና ፓርቲ እና የእኩልነትና የነጻነት ፓርቲ ናቸው።

የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

  1. የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ህወሃት በሀገር መከለከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት እጅግ አሳፋሪ፣ የሚወገዝና መታለፍ የሌለበት ተግባር ነው።

የፌደራል መንግስትና የሀገር መከላከያ ኃይላችን በፅንፈኛውና ካሃዲው ህወሃት ላይ እየወሰደ ያለውን ተመጣጣኝና ተገቢ እርምጃን የሚደግፉ ሲሆን የፌዴራል መንግስት የህወሓትን አገዛዝ ማስወገድ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  1. ፓርቲዎቹ ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይም በሶማሊ ህዝብ ላይ ለ27 ዓመታት በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳትና ጥፋት በመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን የሶማሊ አርብቶ አደር ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ አድርሰዋል።

የፌዴራል መንግስት ይህንን ያደረሱት የህወሓት ቡድን ለህግ እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  1. የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋና ሰላምና ደህንነቱ እንዲጠበቅ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር ጎን በመቆም ሙሉ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
  2. ፓርቲዎቹ የሶማሊ ክልል ህዝብ በክልሉ የሚኖሩ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና የተለያዩ እምነት ተከታዮችን በሰላምና በፍቅር፣ የአብሮነት መኖር ባሻገር ወንድማማችነትና መልካም ጉርብትናን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

(EBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top