Connect with us

በራስ መንገሻ ጊዜ የነበረው ታሪክ በህወኃት ሊደገም ይችላል

በራስ መንገሻ ጊዜ የነበረው ታሪክ በህውኃት ሊደገም ይችላል
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በራስ መንገሻ ጊዜ የነበረው ታሪክ በህወኃት ሊደገም ይችላል

በራስ መንገሻ ጊዜ የነበረው ታሪክ በህወኃት ሊደገም ይችላል

~ ይኸ የውሸት ጋጋታና ጉራ እስከ መቼ ይዘልቅ ይሆን!!? 

(ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

የትግራይ ፖለቲከኞችንና አንዳንድ ምሁራንን እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂ ነን ባይ ግለሰቦችን ውሸትና ጉራ ስመለከት ሁለት ታሪካዊ ፍጻሜዎች ከፊቴ ላይ እየመጡ ድቅን ይሉብኛል፡፡ እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ከእነሱ በስተቀር ጀግና እና የሰለጠነ ሰው የሌለ ይመስላቸዋል ብቻ ሳይሆን ትግራይ ክልል ውስጥ የተሰራው የጋራ ታሪክና ስልጣኔ ሁሉ የእነሱ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡

ለዚህም ነው ሁሉንም ነገር የእነሱ አድርገው በመውሰድ ብቻ ሳይወሰኑ ሞቅ ሲላቸው አማራ ታሪካችንን ሰረቀ እስከማለት የሚደርሱት፡፡

እኔ ግን እላለሁ፣ ትግራይ ውስጥ አገውና አማራን ያላሳተፈና በአማራ ያልተመራ ታሪክና ስልጣኔ የለም፣ ለዚህም ሁለት ምሳሌዎችን ብቻ ላንሳና እውነታውን ላሳይ፣ የአክሱም ስልጣኔ መነሻው አክሱምና አካባቢው ቢሆንም ታሪኩም ሆነ ስልጣኔው የተሰራው ገና ትግራይ የሚባል ህዝብ ባልተፈጠረበት በአማራ አያቶች እና አገዎች አማካኝነት የተከናወነ ደማቅ ታሪክ ነው፡፡

እነዚህ ደፋሮች ግን አክሱም አሁን ላይ ትግራይ በሚባለው ክልል ውስጥ በመገኘቱ ብቻ ታሪኩም በእነሱ ቅድመ አያቶች ብቻ የተሰራ ይመስላቸዋል፡፡

ሌላኛው የአድዋ ድል ጉዳይ ነው፣ ከትላንት ወዲያ ዶ/ር ደብረጺዮን መግለጫ ሲሰጥ ትግራይ ለአሀዳዊያን መቀበሪያቸው ትሆናለች፣ የጀግንነት ታሪክ እንዳለን ይታወቃል፣ ለዚህም አድዋ የኛ ነው የሚል ዲስኩር አሰምቷል፡፡ የእነዚህ ሰዎች ችግር ታሪክን አለማወቅ ብቻ አይደለም፣ ውሸትና ክህደትም በደማቸው ውስጥ ሰርጾ የሚገኝ ባህላቸው መሆኑ ጭምር እንጂ፡፡

እነሱማ አድዋን ብቻ ሳይሆን መቀሌን ጭምር ለቀው በመሸሻቸው አይደለም እንዴ እምየ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ብለው የደረሱላቸው፡፡

የአድዋ ድል ታሪክ እንደሚያመለክተው የመልሶ ማጥቃት ጦርነቱ የተጀመረው አምባላጌ ላይ ነው፣ ይህም የሆነው ትግራዮች የጣሊያንን ግስጋሴ ማስቆም ሲያቅታቸው አድዋንና አካባቢውን ብቻ ሳይሆን መቀሌን ጭምር ለጣሊያ አስረክበው በመሸሻቸው ነው፡፡ እናም ጀግናው የእምየ ምኒልክ ሰራዊት የጣሊያንን ዘመናዊ ጦር ከአምባላጌ ጀምሮ እየጠራረገ በመሄድና በእቴጌ ጣይቱ ብልሀት መቀሌን ያለምንም ኪሳራ በማስለቀቅ አድዋ ላይ ለተገኘው ድል ጉልህ የሆነ አስተዋጽኦ በማድረጓ ነው ፡፡

በነገራችን ላይ በአድዋ ውጊያ ላይ ከተሳተፈው በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ጦር ውስጥ ከትግራይ የተሻለ ተሳትፎ አደረገ የሚባለው የራስ አሉላ አባ ነጋ ሰራዊት ከ3000 አይበልጥም ነበር፡፡ በዚህ ውጊያ ብቻ ሳይሆን በመተማው ውጊያም ጭምር ትልቅ ሚና የነበራቸው የወሎው ራስ አሊ የኋለኛው ንጉስ ሚካኤል ብቻ በአስር ሽዎች የሚቆጠር ሰራዊት ይዘው ነበር የተሳተፉት፡፡

የእነ ራስ መኮንንና ሌሎችም ራሶች ሰራዊት ቁጥር ሲታይ ደግሞ ከራስ አሉላና ባሻይ አውኣሎም በስተቀር የትግራይ ደጃዝማቾች  ያን ያህል ጉልህ ሚና አልነበራቸውም፡፡

እናም እባካችሁ የማይሆን ነገር እየተናግራችሁ እኛንም አታናግሩን፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሆነ በግልጽ የሚታወቅ ነው፣ ማን ማንን እንዳስገደለ፣ ማን አገርን ለመሸጥ ሲደራደር እንደነበረና ሀገር ሲዘርፍ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እዚህ ላይ የራስ መንገሻ ዮሀንስን ታሪክ በአጭሩ አስታውሼ ጽሁፌን ልጨርስ፣ አጼ ዮሀንስ በመተማው ውጊያ ቆስለው ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ንግስናቸውን ለወንድማቸው ልጅ ራስ መንገሻ እንዳወረሱ ተናዘዙ፣ ሆኖም የትግራይ መኳንንትና መሳፍንት ለምን መንገሻ በማለት መስማማት ባለመቻላቸው ወዲያውኑ ሳይነግሱ ቀሩና እምየ ምኒልክ ንጉሰ ነገስት መሆናቸውን አወጁ፡፡ 

ሆኖም ራስ መንገሻ ለንጉሰ ነገስት ምኒልክ አልገዛም አለ፣ ከዛም እምየ ምኒልክ ለወሎው ራስ አሊና ለሀረርጌው ራስ መኮንን ራስ መንገሻን በመያዝ አምጡልኝ ብለው በማዘዛቸው ሁለቱ ራሶች ትግራይን ለመቆጣጠር ወደ ስፍራው ሲሄዱ ራስ መንገሻ ሸሽቶ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ተገኘና ተማርኮ በግዞት መልክ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ተደረገ፡፡

ትግራይም በራስ መኮንን ለተወሰነ ጊዜ እንድትተዳደር ተደረገ፡፡ አሁንም ይኸ አውነተኛ ታሪክ ሊደገም እንደሚችል ይገመታል፣ አቅምን አውቆ መኖር ደግ ነው ታላቅ ችሎታ ነው ያለው ማን ነበር?

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top