Connect with us

ፓርላማው ለስድስት ወራት የሚቆየውን የትግራይ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  አጸደቀ

ፓርላማው ለስድስት ወራት የሚቆየውን የትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ
ፎቶ ፡-ፋይል - አዲስ ስታንዳርድ

ዜና

ፓርላማው ለስድስት ወራት የሚቆየውን የትግራይ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  አጸደቀ

ፓርላማው ለስድስት ወራት የሚቆየውን የትግራይ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማጽደቅ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጣ 7 አባላት ያሉት ግብረኃይል ተቋቁሟል።

ግብረኃይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን ‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረኃይል’’ ተብሎ ይጠራል።

አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፣ እንደየአስፈላጊነቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸው ተጨማሪ አካባቢዎች ግብረኃይሉ በሚያወጣው መመሪያ ይወስናሉ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ በየጊዜው ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ይሆናል።

EBC

(ፎቶ ፡-ፋይል – አዲስ ስታንዳርድ )

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top