Connect with us

የምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መልዕክት!!

የምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መልዕክት!!
Photo: Social media

ዜና

የምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መልዕክት!!

የምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መልዕክት!!

 

“የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ!…

የክብራችን፣ የሉዓላዊነታችን መለያ የሆነው ሠራዊታችን በተልዕኮ ላይ እያለ በገዛ ወገኑ በከሃዲ ቡድን መሪነት ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡ 

ላለፉት ዓመታት የትግራይ የሕዝብ ደጀን የሉአላዊነታችን መከታ ሆኖ የተሰለፈውን ሠራዊት እንዴት በወገኑ በትግራይ ልዩ ኃይል ጥቃት ይፈፀምበታል? 

ሠራዊቱ በራሱ መደበኛ አሠራር የስምሪት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንኳ “ትታችሁን አትውጡ” እየተባለ ህፃን መንገድ ላይ እየወደቀ፣ ለደጀንነት የቆየውን ኃይል ማጥቃት፤ ታላቅ ክህደት ነው፤ ከባዕድ ወረራ የከፋ የከሃዲነት እርምጃ ነው፡፡ 

ይህ ቡድን ኢትዮጵያን በመከፋፈል የሚፈልገውን በኃይል ለመፈፀም የመጨረሻውን የክህደት እርምጃ ሰንዝሯል፤ ተያይዞም ቡድኑ ልዩ ኃይሉን በማንቀሳቀስ በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ ለማካሄድ ከፍተኛ ርብርብ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

ድርጊቱ የክፋት የመጨረሻው ጥግ እና ጡት ነካሽነት ነው። ስለሆነም መንግስታችንና ሕዝባችን ይህን አሳፋሪ ተግባር ለማክሸፍና የሽንፈት ካባውን ለማከናነብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መረባረብ ይኖርብናል፡፡ 

በዚህ አጋጣሚ የተከበርከው እና የኢትየጵያ ማህፀን የሆንከው የትግራይ ሕዝብ ክሃዲው ቡድኑ መሸሸጊያ አድርጎህ፤ ሀገር የሚያጠፋ ሴራውን እየሠራ መሆኑን ተገንዝበህ፤ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነትህን እንድትወጣ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ 

ከሀዲዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብዙ የጭካኔ ተግባራትን እየፈፀሙ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን አትፈርስም! ከሕዝባችን ጋር ሆነን ሀገራችንን እናሻግራለን!!”

~~~~~~

ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም

አዲስ አበባ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top