ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ህዝቡ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ አሳሰቡ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ!
ኢትዮጵያ አገራችን በብዙ የእርስ በእርስ ጦርነት አልፋለች፡፡ ለዚህም መንግስት እርስ በእርስ ጦርነት እንዳይጀመር በብዙ መንገድ በብዙ ዋጋ መክፈል በትዕግስት ሲያልፍ ቆይቷል፡፡
የህገ መንግስት ጥሰት ሲደረግ ፣የህዝብ ምክር ቤቶች ውሳኔ በንቀት ሲወረወር በተመሳሳይ ቦታዎች ላይ በህእቡ አደረጃጀትና በተለየ መንገድ ጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭትን በመቀስቀስ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ የማድረግ ስራ ሲሰራ ፣የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳይጀመር ሲባል በብዙ ትዕግስት በብዙ ማለፍ ስንሄድበት ቆይተናል፡፡
ይሄ አልበቃ ብሎ በአሁኑ ስዓት ትናንት ለዛሬ አጥቢያ የትህነግ ህውኃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊታችን እና አማራ ክልልን ጥሶ በመግባት ተኩስ ጀምሯል፡፡
ይሄ የትህነግ ህውኃት ቡድን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያውቀው ሀገር የዘረፈ ቡድን ነው፡፡
ሀገር ዘርፏል ብቻ ሳይሆን ህገ መንግስትን ወደ ጎን ትቶ እራሱን ከህግ በላይ በማድረግ የሚፈጽማቸውን እኩይ ተግባራት እንደ ጀብድ እያነሳ የሚያወራ፣ የሚፎክር መንግስት ግን ይህንን ድርጊቱን ሁሉ ህዝብን በማየት በትእግስት ሲያይ የቆየ መንግስት ነው፡፡
ይህንን ትእግስት በብዙ ንቀት ሲመለከተው ቆይቷል፡፡ በእርግጥ ጦርነትን ላለመጀመር የመንግስት ትእግስት ብቻውን በቂ ሊሆን አልቻለም፡፡ አሁን በሌላ ወገን ያለው ጦርነት ናፋቂው ይሄ ትግስት ገብቶት ወደ ጦርነት እንዳንገባ እጅን ካልሰበሰበ በስተቀር ማሰቀረት አልተቻለም ከዚህ የተነሳም መንግስት ተገዶ የገባበት ጦርነት እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረዳው ይገባል፡፡
አሁን ይሄ እየሄደ ያለው ጦርነት ይሁ ቡድን ከራሱ ጋር ብቻ ሳይሆን ከታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ጭምር ቁርኝት በመፍጠር እና ከማንም ይሄን ድርጊቴን ሊያግዝ ከሚችል ከውጭ አካል ጋር ተቀናጅቸ እሰራለሁ እገጥማለሁ ብሎ ሳያፍር መግለጫ ሲሰጥበት የነበረ ነው፡፡
ይህንን ህዝባችን በሚገባ መረዳት አለበት ፡፡ መንግስት ተገፍቶና ተገዶ የገባበት እንደሆነና ጦርነቱም የብሔር ጦርነት አይደለም፤ በሆነ ብሔር መካከል የተደረገ ጦርነት አይደለም በፌዴራል መንግስትና በክልል መንግስትም መካከል የተደረገ ጦርነት አይደለም፡፡
የክልል መንግስት እንዳይባል በክልሉ ውስጥ ህዝብ አለ፣የተለያዩ ተቋማት አሉ፣የግብረሰናይ ድርጅቶች አሉ ብዙ አካላት አሉ፡፡
ህዝብ ህዝባችን ነው፡፡ የትግራይ ክልል የሀገራችን የኢትዮጵያ ሀገራችን አካ ነው፡፡
ነገር ግን እብሪተኛው ቡድን ህውኃት ሊያርፍ አልቻለም፣ትዕግስትም ሊገባው አልቻለም ፣ይባስ ብሎ ወደ ማጥቃት ገብቷል፡፡
ይህንን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ምላሽ መስጠት እና ከህዝቡም ጫንቃ ላይ እንዲወርድ ለማድረግ ተገቢ ስለ ሆነ ነው፡፡
ህዝባችን በየቦታው ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፉን መስጠት ይገባል፡፡
የአካባቢውን ጸጥታ በሚገባ ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን መጠበቅ አለበት፡፡
በተለይም ለየት ያለ እንቅስቃሴ በሚኖርበት ሰዓት ለጸጥታ አካ ሪፖርት በማድረግ ፣በተለይ አዲስ አበባ ላይ ብዙ ጊዜ ሲፎክሩ እንደነበረ፣የተለያዩ አካላትን አስታጥቀው ወደ ከተማዋ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ እንደነበረ፣በመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት ላይ የጦርነት አውድማ ለማድረግ ሲጥሩ እንደነበረና የአዲስ አበባ ህዝብ ግን ከጸጥታው አካል ጋር በመሆን ማክሸፍ ተችሏል፡፡
ነገር ግን አሁንም ተስፋ ቆርጠዋል ማለት አይደለም፡፡
ከተማችንን የእኩይ ተግባራቸው ማስፈጸሚያ ስፍራ ለማድረግ አንዱ ኢላማቸው ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡
ስለሆነም የከተማችን ህዝብ ሳይደናገጥ ተረጋግቶ ስራውን እየሰራ በአካባቢው ላይ የሚደረጉ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን በተለይ በሆቴሎች የሚከራይ ሰዎችን መታወቂያ እና ማንነታቸውን የማይገልጽ እና አጠራጥሪ ነገር ካለ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ እና የጸጥታ አካል ማሳወቅ ይገባል፡፡
የውጪ ዜጎች እንኳን ቢሆኑ ፓስፖርታቸውን በትክክል ኮፒ በማድረግ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የመኖሪያ ቤት የሚከራዩ ፣በብዛት የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በሚመለከቱበት ጊዜ ማንነታቸውን መለየት እንኳን ባይቻል ለፖሊስ ሪፖርት አከራዮችም ቤታቸውን ለማን እንደሚያከራዩ በትክክል ለይቶ ማወቅ መቻል አለበት፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ አደረጃጀት ያሉ የከተማችንን ሰላም ለማስከበር ህዝቡን በማገልገል እየሰሩ ያሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች ከህዝቡ እና ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
በተለይ በሰላም ምክር ቤት የተደራጁ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አባላት፣የታክሲ ተራ አስከባሪ እና የጫኚ እና አውራጅ ማህበራት ፣የፓርኪንግ ሰራተኞች ፣የሀይማኖት ተቋማት፣የብሎክ አደረጃጀት ኮሚቴዎችእንዲሁም የሚዲያ አካላት ከሚመለከተው የጸጥታ አካል ጋር አስፈላጊውን ትብብር የተለየ እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባችዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከፌደራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጊያ ስልክ ቁጥሮችን በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ይፋ ይደረገ ሲሆን ህዝቡም ለመከላከያ ሰራዊት እና ለፖሊስ ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ በኩል የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቼውን ጊዜ በላይ ሌት ተቀን ተቀናጅቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ህብረተሰቡም ከከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ሃላፊነቱን መወጣት ይገባዋል፡፡
በከተማችን የምትኖሩ የትግራይ ተወላጆች! ጦርነቱ በትግራይ ብሄር እና በኢትዮጵያ መካከል ወይም ደግሞ በትግራይ ክልል እና ብልጽግና ፓርቲ ፣ በትግራይ እና በፌደራል መንግስት መካከል አይደለም ፡፡
ጦርነቱ ሰላማዊ መንገዶችን ሁሉ በእብሪተኝነት እንቢ ብሎ የግድ ወደ ጦርነት ከገባው ከህውኃት ቡድን ጋር ነው፡፡
ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን በፍጹም በብሄሩ ወደ ሌላ መንገድ ሳይወስድ ፣ሳይቆዝም እና ለሌላ ጥርጣሬ ሳይገባው ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድም እህቶቹ ጋር በመሆን ይህን እኩይ ተግባር እንዲታገል ፣ሀገሩን ነጻ በማውጣት በኩል ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ!!
ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም