Connect with us

የፌደራል መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠ

የፌደራል መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠ
Photo: ጋሻው ፋንታሁን

ዜና

የፌደራል መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠ

የፌደራል መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠ

 

መግለጫውን የሰጡት የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት የክብራችን መለያ የሆነው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ጥቂት ቡድኖች ክህደት ተፈፅሞበታል፤ ክህደቱ ‹‹ከባዕድ ወረራ የከፋ›› ነውም ብለውታል፤ ቡድኑ የመጨረሻውን የክህደት እርምጃም በወገኖቹ ላይ ፈፅሟል ነው ያሉት፡፡ 

እንደ አቶ ደመቀ ማብራሪያ ግጭቱ በትግራይ ህዝብ እና በቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ወይም እስከታች ባለው የትግራይ ክልል የመንግስት መዋቅር እና በፌደራል መንግስት መካከል የተፈጠረ ሳይሆን በህዝብ ጉያ ራሱን ያደራጀውን ቡድን ስርዓት ለማስያዝ እና ህገ መንግስቱን ለማስከበር የተደረገ እርምጃ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ራሱን ከዚህ ቡድን ነፃ እንዲያወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

በአማራ ክልል ህዝቦች ላይም በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ ለማካሄድ ጥረት ተድርጓል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ድርጊቱ የእናት ጡት ነካሽነቱን ያሳየ ነውም ብለዋል፡፡  

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በሃገሪቱ ያሉ የሃገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና በህዝቦች መካከል ግጭት የማያነሳሱ መረጃዎች እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡ 

እውነተኛውን እና መሬት ላይ ያለውን መረጃ ለኢትዮጵያዊያን ብሎም ለዓለም ህዝብ ማድረስ አለባችሁ ያሉት አምባሳደር ሬድዋን መንግስትም ሁነቱን እየተከታተለ በተደራጀው የተግባቦት ጉዳይ ኮሚቴ አማካኝነት መረጃዎችን ለህዝብ ያደርሳል ብለዋል፡፡ 

(ዘጋቢ፡- ጋሻው ፋንታሁን – አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top