Connect with us

የባንዳ ተግባር!

የባንዳ ተግባር!
Photo: Social media

ዜና

የባንዳ ተግባር!

የባንዳ ተግባር!

(ነብዩ ስሁል ሚካኤል – ከትግራይ ብልጽግና ፓርቲ)

ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን በአንዳንድ ስራ ፈቶች ሳይቀር “ምነው ውትድርናው ተትቶ ገበሬ ተሆነ እንዴ” ተብሎ በክቡር ስሙ እስኪሳለቁ ድረስ የአቅመ ደካማ ገበሬ እናቶችና አባቶች ሰብል ሲሰበስብና የአምበጣ መንጋ መከላከል ስራ ላይ ሲረባረብ ከርሞ ጎኑ ለማሳረፍ ጋደም ባለበት ውድቅት ሌሊት ላይ እንዲህ አይነት የለየለየት የክህደት፣ የሽብር፣ የፈሪና የባንዳ ተግባር እላዩ ላይ መፈፀሙ ከማየት በላይ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ነገር የለም!!

የአንዲት ታላቅ ሃገር ታላቅ ሰራዊት በዚህ ደረጃ በህዝባዊ አጀንዳ ተጠምዶ ባለበት ወቅት በክህደትና በድንቁርና በሰከረ የውስጥ ሃይል ተክዶ ሲጠቃ ምናልባትም በዓለም ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ሳይሆን አይቀርም።

የህወሓት ስርዓት በገዛ ወገን ሰራዊት ላይ ተመሳሳይ ግፍ ሲፈፅም ለመጀመርያውም አይደለም፤ ለምሳሌ የዛሬ 46 ዓመት ግ.ገ.ሓ.ት በተባለ የትግራይ ታጣቂ ሃይል ላይ ተመሳሳይ የክህደት፣ የሽብር፣ የፈሪና የባንዳ ድርጊት መፈፀሙ ይታወሳል።

አሁን ይህ የ46 ዓመት የቆየው የክህደትና የባንዳነት ቡዱን እራሱ በቆሰቆሰው አሳፋሪ አጀንዳ ተጠቅመን ለአንዴና ለመጨረሻ መወገድ አለበት!!

ክብርና ድል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና ለህዝባችን!!

ሙሉ ውድቀት ለእናት አገር ጡት ነካሽ ባንዳዎች!!

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top