Connect with us

አምኒስቲ ብሔር ተኮሩን ጥቃት አወገዘ 

አምኒስቲ ብሔር ተኮሩን ጥቃት አወገዘ
Photo: የጀርመን ድምፅ

ዜና

አምኒስቲ ብሔር ተኮሩን ጥቃት አወገዘ 

አምኒስቲ ብሔር ተኮሩን ጥቃት አወገዘ 

በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ለስብሰባ በአንድ ትምህርት ቤት ዉስጥ እንዲገኙ የተጠሩ አማሮች  በተሰበሰቡበት በጅምላ መገደላቸዉን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ። 

ድርጅቱ መንግሥት ለዜጎች ጥበቃ እንዲያደርግ እና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቆአል ።

 አምነስቲ  የሰብዓዊ ጉዳይ ተመልካቾችን እና የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ብሔር ተኮር በሆነዉ በጉሊሶዉ ግድያ ቢያንስ 54 ሰዎች ሕይወታቸዉን አጥተዋል። 

ባለፈዉ እሁድ አካባቢዉ ላይ የነበረዉ የመንግሥት መከላከያ ሰራዊት ለቆ ከወጣ በኃላ አምነስቲ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA)  ሲል የገለፀዉ  ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን በንፁሐን ላይ መፈፀሙን የዓይን እማኞችን ገልጾ አስቀምጦአል።

 በጥቃቱ ሕጻናት ሴቶች፤ እና አባወራዎች ተገድለዋል፤ መኖርያ ሕንጻዎች መገልገያ ቁሳቁሶች ተቃጥለዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጽ / ቤት የሰሞኑን ጥቃት “ጭካኔ የተሞላበት የሽብር ጥቃት” ሲል መሰየሙን ድርጅቱ በመግለጫዉ አካቶአል።  

በአሁኑ ሰዓት አካባቢዉ ላይ የፀጥታ አካላት ጥብቅ ክትትል እያደረጉ ናቸዉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸዉም ተመልክቶአል።(የጀርመን ድምፅ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top