Connect with us

“ሕግ እያስከበርን ጸጋችንን ወደ ሀብት እንቀይራለን !” የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ታከለ ኡማ

“ሕግ እያስከበርን ጸጋችንን ወደ ሀብት እንቀይራለን !” የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ታከለ ኡማ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

“ሕግ እያስከበርን ጸጋችንን ወደ ሀብት እንቀይራለን !” የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ታከለ ኡማ

“ሕግ እያስከበርን ጸጋችንን ወደ ሀብት እንቀይራለን !” የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ታከለ ኡማ

በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት የኢንቨስትመንት ሀሳብ አቅርበው ሀሳባቸውንም ወደ ተግባር እንዲለውጡ ፈቃድ የተሰጣቸው በርካታ ተቋማት ይገኛሉ፡፡

የማዕድንና ኢነርጂ ሚንስቱሩ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በቅርቡ በተለያዩ ክልሎች እያደረጎቸው ያሉ ጉብኝቶች መሠረታዊ አላማም በማዕድን ልማት ለመሰማራት ጠይቀው ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ለመቃኘትና ስራቸውን ለመመልከት እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ፈጠራ በታከለበት እና ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ ስራቸውን እየከወኑ ያሉ ድርጅቶችን መመልክታቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የተሰጣቸውን ፈቃድ አላግባብ እያባከኑ ያሉ ድርጅቶችን ማስተዋላቸውንም እንዲሁ፡፡

በመስክ ጉብኝቱ መነሻም ሀሳባቸውን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ ወደተግባር እየለወጡ የሚገኙ ድርጅቶችን ማበረታታት እና መደገፍ እንደሚገባ እና ከዚህ ውጪ የተንቀሳቀሱትን ደግሞ ወደ ትክክለኛው መስመር ማስገባት አስፈላጊ እንደሆነ መወሰኑን ነው የገለፁት።

 ከተገቢው መንገድ ርቀው በሄዱት ላይም ሕጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለብትም እንዲሁ።

በመሆኑም የማዕድን ልማት ፈቃድ አውጥተው አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እስካሁን ወደ ስራ ባልገቡ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰድ ይጀመራል ብለዋል ፡፡

በተፈጥሮ ጸጋችን ላይ ተቀምጠን በድህነት የምንማቅቅበት ጊዜ እንዲበቃ ቆርጠን በተነሳንበት ወቅት የማዕድን ልማት ፈቃድ አውጥቶ ሀብት ላይ መተኛትንም ሆነ ያልተገባ አሰራርን አንፈቅድም ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ።

የተፈጥሮ ጸጋችን ለሀገራዊ ኢኮኖሚያችን የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍ እንዲል በማሰብ የማዕድን ዘርፉ የሚመራበት መዋቅር እና ዘመናዊ አሰራር እየቀረጽን ባንለበት በዚህ ወቅት ኃላፊነት የጎደለው እና የሕግ ጥሰት ያለበት ተግባር በዝምታ የሚታለፍ አይሆንምም ብለዋል፡፡

በቅርብ ቀናት ውስጥም ተግባራዊ እርምጃ መወሰድ እነደሚጀመርም ገልፀዋል፡፡

ሕግ እያስከበርን ጸጋችንን ሀብት እናደርገዋለን!

የሀሳቦች ሁሉ መዳረሻ ተግባር ነው፤ ሀሳብ የሚመዘነውም በተግባር ነው ብለዋል ሚንስተሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ተግበራትን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ፡፡ (EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top