Connect with us

የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት በቀን እስከ 30 ሺ ሰዎች እየተሳተፉ ነው

የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት በቀን እስከ 30 ሺ ሰዎች እየተሳተፉ ነው
Amhara Mass Media Agency

ዜና

የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት በቀን እስከ 30 ሺ ሰዎች እየተሳተፉ ነው

የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት በቀን እስከ 30 ሺ ሰዎች እየተሳተፉ ነው

ከጥቅምት 9 እስከ ህዳር 9/2013 ዓ.ም ባለው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት ሀገራዊ ጥሪ ተደርጎ ወደ ስራ ከተገባ ዘጠኝ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ ሀገራዊ ጥሪን የተቀበሉ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችም የዓባይ ህልውና የሆነውን ጣናን ከወራሪ ዓረም ለመታደግ የትብብር ክንዳቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ፡፡

ጣናን ከእንቦጭ አረም ነፃ ለማድርግ ለአንድ ወር የተጀመረው ዘመቻም በታሰበው መንገድ እንደቀጠለ የጣና ሃይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ልማት ጥበቃና ኤጄንሲ ስራስኪያጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው ሳንምንት የስራ ክንውን 30 ሺህ የሚጠጋ የሰው ሃይል ማሰማራት መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ 

በስራው የሚሳተፍ የሰው ሃይልም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የማረም ስራውም በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በእያንዳንዱ ቀን 12 ሺህ የሰው ሀይልን ለማሰማራት የተጀመረው ዕቅድም ስኬታማ እየሆነ ነው ብለዋል ስራአስኪያጁ፡፡ 

በመጀመሪያው ሳምንት በ26 ቀበሌዎች ላይ የዓረም ስራ ሲከናውን በሐይቁ ጥልቀትና በመንገድ ችግር ምክንያት ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች በተያዘው ሳምንት ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ 

ዓረሙን የማሰውገድ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆንን የተናገሩት ዶክተር አያሌው ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተለይ የሳሙና፣የቅባት፣የአልባሳት፣ የሳኒታይዘር እና የህክምና እርዳታ ለስራው እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

(አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top