Connect with us

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይጀመራል

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይጀመራል
Photo: Social media

ኢኮኖሚ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይጀመራል

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይጀመራል

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ከሰዓት በኋላ መካሄድ ይጀምራል።

በድርድሩ ላይ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሃ ጉዳይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።

የድርድር ሂደቱ የሦስቱ አገራት መሪዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የሚካሄድ መሆኑንም አምባሳደር ዲና አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በሦስትዮሽ ድርድሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና መብት ባስከበረ መልኩ ድርድሯን ትቀጥላለችም ብለዋል። የሶስትዮሽ ድርድሩ ስኬታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ ፅኑ ፍላጎት እንዳላትም ቃል አቀባዩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ 

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ፤ እስካሁን በተደረጉት ድርድሮች የደቡብ አፍሪካ፣የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የወከላቸው ባለሙያዎች በታዛቢነት እየተሳተፉ መሆኑ ይታወቃል።

ሦስቱ አገራት በነበራቸው ድርድር የአገራቱ ባለሙያዎች በሕዳሴ ግድብ አሞላል እና ውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ ሲከናወን የነበረው የባለሙያዎች ድርድር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደተረገበት የሚታወስ ነው።

በድርድሩ በቀጣይ የሚኖረውን ሂደት በሚመለከት አገራቱ የድርድሩን ሂደት የሚገልጽ ደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካዋ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ናዴሊ ፓንዶር ለመላክ መስማማታቸው አይዘነጋም።

በወቅቱ ሱዳን የምትሰጠው ማረጋገጫ የሚጠበቅ ሆኖ የሦስትዮሽ ድርድሩ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም ይቀጥላል ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል። የግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር የተቋረጠው በሱዳንና በግብጽ ምክንያት እንደሆነ ኢትዮጵያ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል።

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሲካሄድ የቆየው የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከተካሄደው የበይነ መረብ ውይይት በኋላ መቋረጡ የሚታወስ ነው።(አማራ መገናኛ ብዙሀን)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top