Connect with us

በእምቦጭ አረም ምክንያት የጣና የዓሣ ምርት ቀንሷል

በእምቦጭ አረም ምክንያት የጣና የዓሣ ምርት ቀንሷል
Photo: ሙሉጌታ ሙጨ

ኢኮኖሚ

በእምቦጭ አረም ምክንያት የጣና የዓሣ ምርት ቀንሷል

በእምቦጭ አረም ምክንያት የጣና የዓሣ ምርት ቀንሷል

በእንቦጭ አረም እና ተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከጣና ሐይቅ በዓመት ይገኝ የነበረው የዓሣ ምርት በ1 ሺ 700ቶን መቀነሱ ተገለጸ። እንቦጭ አረም በዓሣ ሀብትና አጥማጆች ሕይወት ላይም በከፍተኛ ደረጃ እያዛባ መሆኑም ተገልጿል።

ከ9ሺ ወደ 7ሺ ቶን መቀነሱ የባህርዳር የዓሣና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል ተመራማሪና የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተዋበ ገልጸዋል፤ በጣና ሐይቅ ላይ የዓሣ አስጋሪዎች ቁጥርና የምርቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም ከሐይቁ የሚገኘው ምርት በከፍተኛ ደረጃ እየነቀሰ ነው።

ተመራማሪ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው እንዳስታወቁት በቅርቡ በተካሄደው ጥናት 5 ሺ ዓሣ አስጋሪዎች በዓመት 7 ሺ 300 ቶን ዓሣ አምርተዋል።

 እ.ኤ.አ በ2013 በፈረንጆች አቆጣጠር 3 ሺ 114 አስጋሪዎች በነበሩበት ወቅት ግን 9 ሺቶን አምርተው ነበር። ይህ የሚያሳያው የዓሣ አጥማጆች ቁጥር እና የምርቱ ተጠቃሚዎች ፍላጎት እየጨመረ ሲሄድ ዓሣ ሀብቱ እየቀነሰ ነው።

ለምርቱ መቀነስ አንዱ ምክንት የእንቦጭ አረም መስፋፋት እንደሆነ ተመራማሪው አመልክተው፤ እንቦጭ በባህሪው በፍጥነት እና በስፋት የሚራባና የሚባዛ መሆኑን አስታውቀዋል።

“አረሙ በቅድሚያ የዓሣ መራቢያ ቦታ ይይዛል፣ የዓሣ ዕንቁላልም ለመራባት ምቹ ሁኔታ አያገኝም። በተጨማሪም የፀሐይ ብርሃን ወደ ውሃ ውስጥ እንዳይገባ ያደርጋል። እንቦጩ ሲወገድና ሲሞት በሐይቁ ውስጥ ሌላ ኬሚካል የሚለቅ በመሆኑ በውሃ ውስጥ ያለውን የአየር ዝውውር ያዛባል” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተው እንቦጭ አረም የዓሣ ዋንኛው የመራቢያ ስፍራ የሆነውን ቦታ መያዙን ያመለከቱት ተመራማሪው፣ ይህም በቀጥታ በዓሣ መራባትና ሀብት ዕድገት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ከሐይቁ ምሥራቃዊ ክፍል በእንቦጭ ክፉኛ መጠቃቱን ያመለከቱት ተመራማሪው፤ አካባቢው በታንኳ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ የዓሣ ማስገር ሥራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። ዓሣ ማስገሪያ መረቦች ዓሣ ከመያዝ ይልቅ በእምቦጭ እየተሞሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ኢፕድ እንደዘገበው እንቦጭ ዓሣን ጨምሮ ሌሎች ሃይቅ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት የሚመገቧቸውን ዕጽዋት በማጥፋትቀዳሚ እንደሆነ ያመለከቱት ተመራማሪው፣ ችግሩ የዓሣ ዝርያ እና መጠንን በመቀነስ አደጋ መፈጠሩን ገልጸዋል።

በበጋ ወቅት ጣና ውሃ ሲቀንስ አርሶ አደሩ ጣና ዙሪያ (ባህረ ሸሽ) እርሻ የሚያካሂድ ሲሆን፤ ቀደም ሲል አንድ አርሶ አደር ብቻውን ዜሮ ነጥብ 25 ሄክታር መሬት ለማረስ ይችል ነበር ብለዋል። የእቦጭ አረም ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ግን ዜሮ ነጥብ 25 ሄክታር መሬት ለማረስ 9 ሰው ማስፈለጉን አመልክተዋል። ይህም እንቦጭ እያስከተለ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ተጨማሪ አንድ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የባህርዳር የዓሣና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል በ1992 ዓ.ም የተመሰረተ ማዕከል ሲሆን፤ ዘርፈ ብዙ የምርምር ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

(ሙሉጌታ ሙጨ ~ በኩር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top