ሞሪንጋ (ሽፈራው)
ሞሪንጋ የተሰኘው ቅጠል በህንድ ሀገር እጅግ በጣም አስፈላጊ ሰብል የሆነ ሲሆን ፣በኢትዮጵያ፣በፊሊፒንስ እና በሱዳን እንዲሁም በምስራቅ ፣ምዕራብ፣ደቡብ አፍሪካ ፣ላቲን አሜሪካ፣ድቡብ ኢሲያ እና በሌሎች አንዳንድ አገሮች በስፋት ይገኛል፡፡
ሞሪንጋ ዛፍ (ምተሀተኛው ዛፍ) በሚሰኘው መጠሪያ ስሙ በአለም ላይ እውቅና ያለው የበሽታ ፀር ነው፡፡
ሞሪንጋ ቅጠል ለበርካታ በሽታዎች ፍቱን መድሀኒት እንድሆነ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
- ለደም ማነስ ችግር
- ለአርትራይተስ
- ለሩሲተስ በሽታ
- ለአስም
- ለካንሰር
- ለሆድ ድርቀት
- ለስኳር በሽታ
- ለተቅማጥ
- ለሆድ ህመም
- ለሆድ
- ለአንጀት ቁስለት
- ለአንጀት መታጠፍ
- ለራስ ምታት
- ለልብ ችግር
- ለደም ብዛት
- ለግፊት
- ለኩላሊት ጠጠር እና ለኢንፌክሽን ልዩ የሆነ የተፈጥሮ መድሀኒት ነው፡፡
የሞሪንጋ አዘገጃጀትን
- ሞሪንጋ ቅጠሉን ቀንጥሶ አጥቦ ማድረቅ
- የደረቀውን የሞሪንጋ ቅጠል እንፈጨዋለን
- የተፈጨውን የሞሪንጋ ቅጠል በምንመገበው ምግቦች ውስጥ በቀላሉ እየነሰነሱ መጠቀም
- አልያም በውሃ በጥብጦ መጠጣት ይቻላል፡፡
ሞሪንጋ ቅጠል በተለያየ መንገድ መጠቀም እንችላለን፡፡አንዱ በአፋችን በመመገብ ሲሆን በተጨማሪም ለቆዳችን እንክብካቤ ደግሞ ከላይ በጠቀስነው አዘገጃጀት መሰረት በውሃ አድርገን በቀላሉ የፊታችንን ቆዳ መቀባት ይቸላል፡፡ ሞሪንጋ ለቆዳችን ያለውን ጠቀሜታ ስንመለከት ደግሞ በውስጡ ፀረ-ባክቴሪያ የያዘ እንደመሆኑ መጠን
Ø ከቆዳችን ላይ የሞቱ ሴሎችን በቀላሉ ያስወግዳል፡፡
Ø ጀርሞችን ይገድላል፡፡
Ø ለብጉር መድሀኒት ነው፡፡
Ø የጠቆረ ቆዳን ወደነበረበት የቆዳ ቀለም ይመልሳል፡፡
ሞሪንጋ ለወንድ ልጅ ያለው ጥቅም
ይህ ምትሀታዊ ቅጠል በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ከዛ በተጨማሪም ለወንድ ልጅ በተለየ መልኩ ጥቅሙ ይጎላል ፡፡
ይህን ቅጠል ወንዶች በምግብ መልክ ቢጠቀሙት በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘ እንደመሆኑ መጠን የወሲብ ጉዳይ ላይ ጥቅም አለው፡፡ ለወንድ ልጅ ወንድነትን ሲያጎናፅፍ ከዛም በተጨማሪ ቫይታሚን ኤ በውስጡ ስለሚገኝ የወንድ የዘር ፈሳሽን በብዛት እንዲመነጭ ያደርጋል፡፡ ቫይታሚን ሲ ከሰውንቱ ወደ ብልቱ የሚዘዋወረውን የደም ዝውውር በተሳካ ሁኔታ እንዲዘዋወር እና ጥንካሬ እንዲኖርው ይረዳዋል፡፡
ሞሪንጋ ለፀጉር ምን ጥቅም አለው
ይህ ተአምራዊ ቅጠል የፀጉርን ይዘትን ጠንካራ ፣ወፍራም እና ጤናማ ፀጉር እንዲሆን ማድረግ ይችላል፡፡ምክንያቱ ደግሞ በውስጡ በያዘው አልሚ እና የሚያጠነክር ንጥረ ነገር ነው፡፡
ውስጡ የሚገኘውን ንጥረ ነገር ስንመለከት ደግሞ እንደ ፕሮቲን፣ቫይታሚኖች ፣አሲድ ፣ ዚንክ፣ ፎስፈረስ፣ ማግኒዥየም እና የመሰሉ ንጥረ ነገሮች ስለሚገኝ በቀላሉ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ይረዳናል፡፡
ሞሪንጋ ለእርግዝና ምን አይነት አስተዋፅኦ አለው
ሽፈራው በሁሉም የእርግዝና ወቅት ከቅድመ ወሊድ አንስቶ ፤እርግዝና እስከ ድህረ ውልደት ድረስ ጥቅመ ብዙ ነው፡፡
- ቅድመ ወሊድ በተመለከተ ለማርገዝ ጥረት እያደረግሽ ከሆነ ሞሪንጋ በውስጡ ያለው ንጥረ ነገር የማራቢያ ስርአቱን በተፈለገው እና ጤናማ በሆነ መንገድ እርግዝና እንዲከናወን ይረዳል፡፡
- በእርግዝና ወቅት ደግሞ እናት እና ልጅ ጤናማ የሆነ ቆይታ እንዲኖራቸው በውስጡ በሚገኘው ንጥረ ነገር አይረን ፣ካልሲየም ይረዳቸዋል፡፡
- ከወሊድ በኋላም ቢሆን ይህ ታምራዊ ቅጠል የእናትየዋን ሰውነት በቶሎ እንድያገግም እና የጡት ወተት በደንብ እንዲኖራት ያደርጋል፡፡
ነገር ግን ሞሪንጋ ጥቅም እንዳለው ቢታወቅም በእርግዝና ወቅት ላይ የህክምና ባለሙያ እማከርን የህክምና ባለሙያው በሚነግረን መጠን መውሰድ ይኖርብናል፡፡
ሞሪንጋ ጉዳት ያስከትላልን
ማንኛውም ነገር ጥቅም እንዳለው ሁሉ አብዝተን ስንጠቀም የሞሪንጋም ቅጠል እንደ ሌላው ጉዳት አለው ፡፡ነገር ግን ከጉዳቱ ጥቅሙ ስለሚያመዝን ብንጠቀመው ይመረጣል፡፡
- አነስተኛ የልብ ምት እንዲኖር ያደርጋል፡፡
- ዝቅተኛ የደም ግፊት
- በኩላሊት እና በጉበት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡
(ምንጭ፡- www.healthline.com,www.asbestos.com….)