Connect with us

ቁጠባን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክር እነሆ

ቁጠባን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክር እነሆ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ኢኮኖሚ

ቁጠባን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክር እነሆ

ቁጠባን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክር እነሆ

አንዳንዴ ገንዘብ የመቆጠብ አስቸጋሪው ጉዳይ መጀመሩ ነው፡፡ የሚከተሉትን ሰባት ነጥቦች  በቅደም ተከተል መተግበር ገንዘብ ለመቆጠብ ያግዛል፡፡ 

  1. ወጪን መመዝገብ

ቁጠባን ለመጀመር የመጀመሪያው ተግባር ወጪን ማወቅ ነው፡፡ በወር ውስጥ ከሻይ ቡና ጀምሮ ለቲፕ አስከምንሰጠው ሳንቲም ደረስ እያንዳንዷን ወጪ በአግባቡ መዝግቦ መያዝ፡፡ 

  1. ለቁጠባ በጀት መመደብ

ወርሃዊ ወጪ ከታወቀ በኋላ፣ የወጪ ዝርዝሩን በአይነት በመከፋፈልና በማደራጀት ወደበጀት መቀየሩ ቀጣይ ተግባር ነው፡፡ በጀቱ ወጪያችን ከገቢያችን አንፃር ምን እንደሚመስል ያሳያል፡፡ ይህም በቀጣይ የተጋነነና አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት ገቢና ወጪን ለማጣጣም ይረዳል፡፡ አዘውትረው የማይመጡ ነገር ግን የማይቀሩ ወጪዎች መዘንጋት የለባቸውም፡፡

የበጀት ዝርዝሩ ላይ ቢያንስ የገቢን ከ10-15 በመቶ ለቁጠባ መመደብ፡፡

  1. ለወጪ ቅነሳ የሚረዱ መንገዶችን መፈለግ  

ወጪ ከፍተኛ ሆኖ የሚፈለገውን ያክል መቆጠብ የማያስችል ከሆነ ወጪ ቅነሳ ላይ መስራት ግድ ሊሆን ይችላል፡፡ 

  • እንደ መዝናኛ እና ከቤት ውጪ መመገብን የመሳሰሉ መሠረታዊ ያልሆኑና ወጪያቸው ሊቀነስ የሚችሉትን መለየት፡፡ 
  • የስልክ የአየር ሰዓት ግዢ የመሳሰሉ ቋሚ የሆኑ ወጪዎችን መቀነስ፡፡ 
  1. የቁጠባ አላማ ማስቀመጥ 

የቁጠባ አላማን ማስቀመጥ ለቁጠባ ወሳኙ መንገድ ነው፡፡ ቁጠባ ለምን አላማ ሊያስፈልገን እንደሚችል በማሰብ መጀመር – ጋብቻ መፈፀም አስበናል? ትምህርታችንን መቀጠል እንፈልጋለን? መኪና ወይም ቤት መግዛት እንመኛለን? ጉዞና መዝናናት አስበናል? ለእርጅና ዘመናችን ጥሪት መቋጠር እንፈልጋለን? 

አላማን ከለዩ በኋላ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግና ለቁጠባው የሚወስደውን ጊዜ ለይቶ በማወቅ የአጭር፣ የመካካለኛ እና የረጅም ጊዜ የቁጠባ እቅድ ማውጣት ቀጣዩ ሥራ ነው፡፡

  1. ቅደም ተከተል ማስቀመጥ

ከገቢና ወጪ ቀጥሎ የቁጠባ አላማ የቁጠባ በጀት ድልድል ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው፡፡  ረጅም ጊዜ የሚወስዱ የቁጠባ አላማዎችን ባለመዘንጋት ነገር ግን ቅድሚያ መስጠት ያሉብንን የቁጠባ አላማዎች በመለየት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ 

  1. ትክክለኛውን የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት መምረጥ

እንደቁጠባ አላማና የሚወስደው ጊዜ ተስማመሚውን የቁጠባ አገልግሎት አይነት ለይቶ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ አላማዎች የሚውሉ የቁጠባ አገልግሎት አይነቶችን ከተሻለ ወለድ እና ሌሎች ጥቅሞች ጋር ይሰጣል፡፡ 

  1. የቁጠባውን እድገት መከታተል

በየወሩ የበጀት አፈፀፀምን በመከታተል በእቅድ መሠረት እየሄደ መሆን አለመሆኑን ማረጋጋጥና የተፈጠረ ልዩነት ሲኖር በአፋጣኝ ማረም ተገቢ ነው፡፡ ቁጠባ እየገባን እና ቁጠባችን እያደገ ሲሄድ የበለጠ ለመቆጠብ እና አላማችንን ቶሎ ለማሳካት ተነሳሽነታችን ይጨምራል፡፡(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top