Connect with us

ትራምፕ “ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች” ሲሉ ተናገሩ

ትራምፕ "ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች" ሲሉ ተናገሩ
Photo: Social media

ዜና

ትራምፕ “ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች” ሲሉ ተናገሩ

ትራምፕ “ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች” ሲሉ ተናገሩ

ትራምፕ ኢትዮጵያ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ስምምነትን ጥላ መውጣት አልነበረባትም አሉ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ሃምዶክ እና ከእስራኤሉ ቤንያሚን ኔይተናሁ ጋር በቀጥታ የስልክ ውይይት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ነው።

የቀጥታ የስልክ ውይይቱ ሲካሄድ ጋዜጠኞች ተገኝተው የነበረ ሲሆን የሱዳኑም ጠቅላይ ሚኒስትር ግድቡን በሚመለከት በቅርቡ በሶስቱ አገራት መካከል ስምምነት ይደረሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሁለቱ መሪዎች የደወሉት ሱዳንና እስራኤል ግንኙነታቸውን ለማሻሻል መስማማታቸውን በማስመልከት ነበር።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር “በቅርቡ ስምምነት ላይ እንደርሳለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ያሉ ሲሆን ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት ሁለቱን መሪዎች የሚያናግሩት ትራምፕ ግን፣ ለግብጽም ተመሳሳይ ነገር መናገራቸውን በመጥቀስ ሁኔታው አደገኛ መሆኑን ገልፀው፣ ግብጽ “ግድቡን ታፈነዳዋለች” ብለዋል።

በኋይት ሐውስ የሆነው ምን ነበር?

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ ኢትዮጵያ ወደ ስምምነቱ መመለስ አለባት፤ ግብጽ ብስጭት ቢገባት ልትኮነን አይገባም፤ “ያን ግድብ ልታፈነዳው ትችላለች” ሲሉ ተደምጠዋል።

ትራምፕ ኢትዮጵያ ጥላ ወጣች ያሉት ስምምነት የትኛው ስለመሆኑ ያሉት ነገር የለም።

ሱዳን እና እስራኤል የሰላም ስምምነት መድረሳቸውን በማስመልከት ዛሬ በዋይት ሃውስ ትራምፕ የሁለቱን አገራት መሪዎች ጋዜጠኞች በተገኙበት በስልክ ሲያነጋግሩ ነበር።

ፕሬዝደንት ትራምፕ የሱዳኑን ጠቅላይ ሚንስትርን፤ “በመስመሩ ላይ እያሉ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ እንዴት እየሆነ ነው? በማለት የጠየቁ ሲሆን ግድቡ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ አገራት እንዳይፈስ መከልከሉን ሲናገሩ ይደመጣል።

አክለውም ከግብጽ እና ኢትዮጵያ ጋር ሶስተኛ ወገን ሆናችሁ ጉዳዩን በቅርብት እየተመለከታችሁ ነው። ከምን ደረሰ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ትራምፕ ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሳይጠብቁ፤ “ስምምነት እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም። ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። እንዴት እየሆነ ነው? ምን ያውቃሉ?” ሲሉ ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር በድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል።

በዚህ መካከል በስልክ መስመር ላይ የሚገኙት የእስራኤሉ  ጣልቃ ሲገቡ፤ ትራምፕ ጥያቄውን ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ያቀረቡት መሆኑን ተናግረዋል።

ትራምፕ “ለዚህ ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚፈልግ [የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር] አይመስለኝም” ካሉ በኋላ ፈገግ ብለዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር፤ “ሁሉንም ሊጠቅም የሚችል ሁሉን አካታች ስምምነት በቅርቡ እንደርሳለን ብለን እናስባለን” በማለት የመለሱ ሲሆን ትራምፕ ተቀብለው፤ “እንደዛ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ስምምቱን አፍርሰዋል። ይህን ደግሞ ከፍተኛ አጣብቂኝ ፈጥሯል። ግብጽ በዚህ ሁኔታ መኖር አትችልም። ልታፈነዳው [ግብጽ] ትችላለች። ደግሜ እናገራለሁ ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች” ሲሉ ተደምጠዋል።(BBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top