Connect with us

14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶች ታግደዋል

14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶች ታግደዋል
Arts Tv World

ዜና

14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶች ታግደዋል

14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶች ታግደዋል

ህብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የአፍላ ቶክሲን /Aflatoxine/ የተገኘባቸውን 14 የለውዝ ቅቤ ምርቶችን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ባደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ አማካኝነት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ምርቶቹ ከፍተኛ አፍላ ቶክሲን /Aflatoxine/ እንደተገኘባቸው ገልጿል፡፡

ለውዞቹን የሚያመርቱ ተቋማትም ላይ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አምራቾቹን ለማግኘት አለመቻሉንም  አስታውቋል፡፡

የሚመለከተቻው የቁጥጥር አካላት ምርቶቹ  ከገበያ ላይ በመሰብሰብ እንዲያስወግዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ያገዳቸው የለውዝ ቅቤዎች፡- 

ምስራቅ የለውዝ ቅቤ

ሳራ የለውዝ ቅቤ

ዳና የለውዝ ቅቤ

ሰገን የኦቾሎኒ ቅቤ

አርሂቡ የለውዝ ቅቤ

ረጃት የለውዝ ቅቤ

ኢትዮ የለውዝ ቂቤ

ጽዮን የለውዝ ቅቤ

ማሀሩን የኦቾሎኒ ቅቤ 

ላቪሊ የሎዝ ቂቤ 

እናት የሎዝ ቅቤ 

ኤ.ኤፍ የሎዝ ቅቤ 

መና የኦቾሎኒ ቅቤ

ሂር የለውዝ ቅቤ     መሆናቸውን  አስታውቋል፡፡(አርትስ ቲቪ)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top