Connect with us

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጉራፈርዳ ናቸው

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጉራፈርዳ ናቸው
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ዜና

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጉራፈርዳ ናቸው

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጉራፈርዳ ናቸው

ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና ሌሎችም የማህበረሰብ ተወካዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ጥቅምት 8 እና 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 31 ሰዎች መሞታቸውን፣በአምስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ 1 ሺ 480 በላይ አባወራዎች ተፈናቅለው በቢፍቱ ከተማ መጠለላቸውን ፋና መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡

 ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን በተወሰደ እርምጃ 16 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት ዘገባው ያሳያል፡፡

በጉራፈርዳ ወረዳ በ2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሁኔታ በተፈጸመ ጥቃት ከ20 ሺ በላይ ወገኖች መፈናቀላቸው አይዘነጋም፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top