Connect with us

ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 839 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ 

ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 839 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
Photo: Social media

ኢኮኖሚ

ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 839 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ 

ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 839 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ 

ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ለውጭ ገበያ  ከቀረበቻቸው ምርቶቿ  839  ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን  የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ አካላት የ2013 በጀት ዓመት  የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ  የምክክር  መድረክ  በቢሾፍቱ  እያካሄዱ ነው።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመድረኩ ላይ እንዳስታወቁት  ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ ዘርፍ  839 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር  ገቢ  ተገኝቷል።  አፈጻጸሙም ከእቅዱ 95  በመቶ  ተሳክቷል ብለዋል።

ከአጠቃላይ ለውጭ ገበያ ተልኮ ከተገኘው ገቢ ከግብርና የወጪ  ምርቶች  ብቻ 541  ሚሊዮን  ዶላር የተገኘ ሲሆን ቀሪው  ከማዕድንና ማምረቻ ኢንዱስትሪው  ዘርፈ የተገኘ ነው።

ባለፉት ሶስት ወራት  የንግድ ስርዓቱን ማዘመን፣ የገበያ ዋጋን ማረጋጋት እና የአገር ውስጥ ምርትን  ማሳደግ ላይ  በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ መላኩ ተናግረዋል። የንግድ ሥርዓቱን ጠንካራ  እና ዘመናዊ  ለማድረግ በትኩረት እየተሰራም  ነው  ብለዋል።

ሚኒስቴሩ  እና ተጠሪ  ተቋማት የሶስት ወራት  እቅድ አፈጻጸማቸውን  በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።(EBC)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top