Connect with us

ቅዱስ ሲኖዶስ በተቃርኖ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎችን በማነጋገር ለሰላም እንዲማፀናቸው ፓትያርኩ ጠየቁ

ቅዱስ ሲኖዶስ በተቃርኖ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎችን በማነጋገር ለሰላም እንዲማፀናቸው ፓትያርኩ ጠየቁ
Photo: Social media

ዜና

ቅዱስ ሲኖዶስ በተቃርኖ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎችን በማነጋገር ለሰላም እንዲማፀናቸው ፓትያርኩ ጠየቁ

ቅዱስ ሲኖዶስ በተቃርኖ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎችን በማነጋገር ለሰላም እንዲማፀናቸው  ፓትያርኩ ጠየቁ

  • አኹን እየተካሔዱ ያሉት የግጭቶች አቅጣጫዎች የሚመስሉ ትንኰሳዎች፣ የኋላ ኋላ ምን ያህል ፀፀት እንደሚያስከትሉ፣ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ድብቅ ምስጢር አይደሉም፤
  • በሰዎች መካከል ሰላም ከሌለ፣ ቤተ ክርስቲያንም ተጎጂ ናት፤ ልጆቿ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በሰላም ዕጦት ሕይታቸውንና ንብረታቸውን ሲያጡ ከማየት የበለጠ የቤተ ክርስቲያን ጥቃት የለም፤
  • ቅዱስ ሲኖዶስ የኹሉም በጎች እኩል ጠባቂ ነውና፣ የገለልተኝነት እና የማእከላዊነት አቋሙን ጠብቆ፣ የኹሉም ወገን አባትነቱን ሳያዛንፍ፣ ለልጆቹ ዕርቅ እና ሰላም መረጋገጥ፣ ኹሉንም በአባታዊ ፍቅር እያቀፈ ማስታረቅ፣ በዚኽ ዓመት የመጀመሪያ ተግባሩ ማድረግ ይኖርበታል፤
  • ይህ ዓቢይ ጉባኤ፣ እንደካኹን ቀደሙ፣ ኮሚቴ አቋቁሞ መለያየት ሳይኾን፣ የሀገር ሰላም ጉዳይ ቀጥታ ይመለከተናል፤ በሚል ቅን መንፈስ፣ በተቃርኖ ያሉ ኃይሎችን፣ በግንባር በማግኘት እና በማነጋገር፣ የአንድ ሰው ሕይወት እንኳ እንዳይጠፋ፣ ኹሉም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠንክሮ መማፀን አለበት፤
  • የኹሉም ምርጫ፣ ውይይት እና ውይይት ብቻ እንዲኾንም በርትቶ በመሥራት ኹሉንም ማሳመን አለበት፤ ከዓቅሙ በላይ ከኾነም፣ ልምዱ እና ጥበቡ ያላቸው፣ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ገለልተኛ ወገኖችን በማሳተፍ የዕርቁ እና የሰላሙ ተልእኮ ግብ እንዲመታ ማድረግ አለበት፤ ይህ ተግባር፣ ወቅቱ ሓላፊነት የጣለበት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ (ሐራ ተዋህዶ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top