Connect with us

በኢትዮጵያ 420 ሺህ ሔክታር ላይ የሰፈረ ሰብል በአንበጣ መንጋ ጥቃት ደርሶበታል

በኢትዮጵያ 420 ሺህ ሔክታር ላይ የሰፈረ ሰብል በአንበጣ መንጋ ጥቃት ደርሶበታል
BBC NEWS | አማርኛ

ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ 420 ሺህ ሔክታር ላይ የሰፈረ ሰብል በአንበጣ መንጋ ጥቃት ደርሶበታል

በኢትዮጵያ 420 ሺህ ሔክታር ላይ የሰፈረ ሰብል በአንበጣ መንጋ ጥቃት ደርሶበታል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ጥቃት ያደረሰው በ240 ወረዳዎች መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ሰኞ እለት በተካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው አካባቢዎች አፋር፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መሆናቸውን ገልፀዋል።

በእነዚህ የአንበጣ መንጋ ጥቃት የደረሰባቸው አካባቢዎች በጥቅሉ 240 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በእነዚህ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል ደግሞ በ705 ቀበሌዎች ላይ ብቻ አንበጣው ጥቃት ማድረሱን ገልፀዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች በድምሩ 4 ሚሊየን ሄክታር ታርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዚህም መካከል ጥቃት የደረሰበት 420ሺህ ሔክታር ገደማ መሆኑን ተናግረዋል።

ከውጪ ኬሚካል የሚረጩ አውሮፕላኖችን እና ድሮኖችን [ሰው አልባ አውሮፕላን] ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሂደቱ ግን አልጋ ባልጋ አለመሆኑን አመልክተዋል። (BBC NEWS | አማርኛ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top