Connect with us

ማህበራዊ ህክምና!…

ማህበራዊ ህክምና!...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ማህበራዊ ህክምና!…

ማህበራዊ ህክምና!…

“ተከፋፍሎ መናቆሩ እስከ ቀበሌ እና ጎጥ ወርዷል”

(ታዬ ደንደአ ~የኦሮምያ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር)

“ለ 27 ዓመታት የተንሰራፋዉ ግፈኛ ስርዓት አሁን ሞቷል። ነገር ግን ሦስት ከባባድ ጠባሳዎችን ጥሎ አልፏል። አንድ ተቋማትን በእጅጉ አድቋል። 

ህዝባዊ ተቋማት በአብዛኛዉ በአቅመ-ቢሶች እና በመርህ  አልባዎች ተሞልቷል። በበርካታ መስርያ ቤቶች ህዝብን የሚያንገላታ እንጂ በኃላፊነት የሚያገለግል መንምኗል። 

ሁለት ማህበራዊ እሴቶቻችንን ክፉኛ አናግቷል። ግለኝነት ከሚገባዉ በላይ የገዘፈ ይመስላል። ይሉኝታ ጠፍቶ ሌብነት እና ዋሾነት “የአራዳ ልጅ” ያስብላል። ሦስት አገራዊ እይታን ሸርሽሯል። 

ብሔር የሁሉም ነገር መለኪያ ሆኖ ፍትህንና ስብዕናን ተጭኗል። ደግሞ ቡድናዊ መገፋፋት በብሔር ደረጃ ብቻ መች ይቆማል? ተከፋፍሎ መናቆሩ እስከ ቀበሌ እና ጎጥ ወርዷል! ይህ ለዴሞክረሲ ግንባታ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ህልውናም ጠንቅ ይሆናል! ጠንክረን ለመሻገር መደመር ግድ ይለናል! ለመደመር ደግሞ ጥሩ ማህበራዊ ህክምና ያስፈልገናል! በዚህ ረገድ ከሚዲያዎቻችንና ከማህበራዊ ሳይንስ ምሁራኖቻችን ብዙ ይጠበቃል! ከሁሉም በላይ ግን በማንበብና በማዳመጥ ራሳችንን ማከም ይጠቅማል!”

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top