Connect with us

ሰው አልባ  አውሮኘላን (ድሮን) በዕርዳታ ተገኘ

ሰው አልባ አውሮኘላን (ድሮን) በዕርዳታ ተገኘ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

ሰው አልባ  አውሮኘላን (ድሮን) በዕርዳታ ተገኘ

ሰው አልባ  አውሮኘላን  (ድሮን) በዕርዳታ ተገኘ

የጀርመን መንግስት ለግብርና ሚኒስቴር  ሶስት የሰው አልባ በራሪ ቁሶችን (ድሮኖች) ድጋፍ አደረገ።

የግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም እና የአደጋ መከላከል ሥራዎችን  ለማዘመን የሚያስችሉ ሶስት የሰው አልባ በራሪ ቁሶችን (ድሮኖችን)  ከጀርመን መንግስት በድጋፍ አገኘ።

የአንዱ ሰው አልባ  በራሪ ቁስ(ድሮን) ዋጋ 28 ሺህ ዩሮ  መሆኑን በርክክብ ስነ  ስርዓቱ ላይ  ተገልጿል።

ድሮኖቹ በአንድ በረራ ያለማቆራረጥ ለ90 ደቂቃ ያህል የመብረር አቅም ያላቸው  ሲሆን በአንድ ጊዜም 7 መቶ ሄክታር  መሬት  የሚሸፍን መሬት የምስል መረጃን በማንሳት መያዝ ይችላሉ ተብሏል።

እነዚህ ሰው አልባ በራሪ ቁሶች ድጋፍ  ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በማሰባሰብ ውጤታማ ስራዎችን ያከናውናሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

በተለይም በተደጋጋሚ ድርቅ እያጠቃቸው ለሚገኙ አፋርና ሱማሌ ክልሎች ወቅታዊ መረጃዎችን በመላክ መንግሰት የአደጋ መከላከል ስራውን እና ሌሎች መፍትሄዎችን  እንዲሰጥ አቅም እንደሚፈጥርለት በርክክብ  ስነ  ስርዓቱ ላይ ተመልከቷል።

የጀርመን መንግስት ያደረገው ድጋፍ  የሁለቱን መንግስታት  ወዳጅነት ያጠናክራልም ብለዋል።

ሰው አልባ በራሪ መሳሪያዎችን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር  ስቴፈን ኡር ለግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን አስረክበዋል ።

በድጋፍ  መልክ የተሰጡት በራሪ ቁሶች የኢትዮጵያን የደህንነትና የሲቪል አቨየሺን ስታንዳርድ ያሟሉ መሆናቸም ተመልክቷል ።

በርክክብ ስነ ስርአቱ ወቅት  የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አመራሮች ተገኝተዋል።(EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top