Connect with us

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30 የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ ያደርጋሉ

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30 የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ ያደርጋሉ
Amhara Mass Media Agency

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30 የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ ያደርጋሉ

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያደርጉ ተገለፀ፡፡

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያደርጉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ የኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30 ቀን 2013ዓ.ም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ፕሮቶኮል መሠረት በተካሔደው የተቋማት ድጋፍና ምልከታ ውጤት በአንድ አንድ ተቋማት የታዩት ክፍተቶች በፍጥነት ተሟልተው በግልጽ መርሃ-ግብር ለተማሪዎች ቅበላ እንዲደረግም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴዔታ ዶክተር ሙሉ ነጋ የተቋማቱን የቅድመ ቅበላ ዝግጅት ዳሰሳ ውጤት በተመለከተ እንዳሉት ኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ የመማር ማስተማር ስራን ማስቀጠል ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው በሀዋሳ ከተማ የተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት ግምገማ ላይ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና የሠላም ጉዳይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ባለድርሻ አካላት፣ የተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች የበለጠ ተቀራርበው በቅንጅት በመስራት ተቋማቱ ሠላማዊ፣ ሳቢ እና የከፍተኛ ትምህርት የዓለም አቀፋዊነት (Universal) ባህሪ እንዲኖራቸዉ እና ከተቋቋሙለት ዓላማ ጋር ካልተጣጣሙ ጉዳዮችም እንዲላቀቁ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

ምንጭ :- Amhara Mass Media Agency

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top