Connect with us

ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚቀየርበት ጊዜ ማብቃቱ ተገለጸ

ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚቀየርበት ጊዜ ማብቃቱ ተገለጸ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚቀየርበት ጊዜ ማብቃቱ ተገለጸ

ከመቶ  ሺህ  እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚቀየርበት ጊዜ ማብቃቱን የገንዘብ ሚኒስቴርና የብሄራዊ ባንክ አስታወቁ

ከመቶ  ሺህ  እስከ 1 ሚሊዮን ብር በአዲሱ  የብር  ኖት የሚቀየርበት ጊዜ ማብቃቱን የገንዘብ ሚኒስቴርና የብሄራዊ ባንክ  ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2013 በጋራ በሰጡት መግለጫ  አስታውቀዋል።

እስካሁን ባለው ጊዜ 96 ቢሊየን አዲስ የብር ኖት ወደ ባንኮች መሰራጨቱን የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።

በቅያሬው ወቅት ሀሰተኛ  የብር  ኖቶች ያሰራጩ ህገ ወጦች ያጋጥሙ እንደነበርና እስከ ማተሚያ ማሽናቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውም በመግለጫው ተመልክቷል።

ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት በገጠር የአገሪቱ  አካባቢ ትኩረት ተሰጥቶ ከ100 ሺህ ብር በታች ያለው ቅያሬ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ  ብሔራዊ  ባንክ  አስታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከፌደራል መንግስት  ኮማንድ ፖስት  እና ከክልል  አመራሮች ጋር  በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር  እየተደረገ  መሆኑም ተገልጿል።(ኢቢሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top