Connect with us

ሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን እውቅና አገኘ

ሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን እውቅና አገኘ
ሃይለማርያምና  ሮማን ፋውንዴሽን

ዜና

ሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን እውቅና አገኘ

ሃይለማርያምና  ሮማን ፋውንዴሽን እውቅና አገኘ

~ “ያወጣነው አሳሪ ህግ ተነስቶ ተጠቃሚ በመሆናችን አመሰግናለሁ” አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ያቋቋሙት ፋውንዴሽን ህጋዊ ዕውቅና አገኘ። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በሰርተፍኬት አሰጣጥ ስነ- ስርዓት ወቅት እንደገለጹት የቀድሞው አዋጅ በብዙ መልኩ ገዳቢ የነበረ እና አሁን በተሻሻለው አዋጅ መሰረት በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረጉ በየግዜው አዳዲስ ድርጅቶች እየተቋቋሙ መሆኑን ገልጸው ሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽንም በዚህ ሂደት ተመዝግበው ሰርተፍኬት ለመውሰድ በመምጣታቸው ለሌሎች ተምሳሌት እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

የቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው እኛው ያወጣነው አሳሪ ህግ ተነስቶ ተጠቃሚ በመሆናችን እና ከኤጀንሲው በዚህ ዓይነት መልኩ በአጭር ግዜ አገልግሎት በማግኘታችን ምስጋናዬን እያቀረብኩ የመጀመሪያው መሪ ከስልጣን ወርዶ በድጋሜ ህዝብን ለማገልግል በመታደሌ ኩራት ይሰማኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ድርጅቱ የእናቶችና ህጻናት ጤና እና ስነምግብን 

በማህበረሰብ መካከል ማዳበር፣ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአከባቢ ጥበቃ እና ኢኮቱሪዝም ማስፋፋት እና የሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚል ዓላማ ያለው ‹‹ሃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ›› የተባለ ድርጅት ማቋቋማቸውን ገልጸው ድርጅቱ በቀጣይ ከኢትዮጵያ አልፎ በ Horn of Africa ጭምር ለመስራት ስትራቴጂክ እቅድ መንደፋቸውን አብራርተዋል፡፡(ምንጭ ኤጀንሲው)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top