Connect with us

ቡና ባንክ  የብር ኖቶች ለውጥ ጋር ተያይዞ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገደማ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ቻለ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የብር ኖቶች ለውጥ ጋር ተያይዞ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገደማ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ቻለ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ኢኮኖሚ

ቡና ባንክ  የብር ኖቶች ለውጥ ጋር ተያይዞ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገደማ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ቻለ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ  የብር ኖቶች ለውጥ ጋር ተያይዞ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገደማ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ቻለ

 ~ ባንኩ ለ “ገበታ ለሃገር” እና ለተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክቶች የ11 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል 

ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲሶቹ የመቀየር ስራ ከተጀመረ  በኋላ በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ቅርንጫፎች በተከፈቱ ከ66 ሺህ በላይ አዳዲስ የቁጠባ ሂሳቦች እስከትናንት ጥቅምት 5 ቀን ድረስ ብቻ ወደ 836 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ።

መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ የተጀመረውን  የባለ 10፣ 50 እና 100 ነባር የብር ኖቶች ለውጥና አዲሱን የባለ 200 ብር ኖት የማስተዋወቅ ሃገርአቀፍ እንቅስቃሴ ተከትሎ  ባንኩ በመላው ሃገሪቱ በከፈታቸው 245 ቅርንጫፎቹ አሮጌውን የገንዘብ ኖት በአዲስ የመቀየር እና አዳዲስ የቁጠባ ሂሳብ በማስከፈት ውጤታማ ተግባር ማከናወኑንም ዛሬ በዋና መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው  መግለጫ አብራርቷል።

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት ባንኩ እስከትናንትናው ቀን ድረስ ከብሄራዊ ባንክ የተላኩለትን 966 ሚሊዮን 200 ሺህ አዳዲስ የብር ኖቶች በፍጥነት በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች ወደሚገኙት ቅርንጫፎቹ አሰራጭቷል። 

ባንኩ ነባሮቹን የብር ኖቶቹ  በአዲሶቹ ከመቀየር በተጨማሪ 66 ሺህ 828 አዳዲስ የባንክ ቁጠባ ሂሳቦችን ማስከፈት መቻሉን የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ ይህም ከዚህ በፊት ከነበረው የቁጠባ ሂሳብ አከፋፈት ልምድ ጋር ሲነጻፀር የ49 በመቶ እድገት ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። 

የብር ኖቶች ለውጥ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ በተከፈቱት አዳዲስ የባንክ ሂሳቦች ውስጥ 835 ሚሊዮን 956 ሺህ 863 ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ይህ አፈጻፀም ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ  ጋር ሲነጻፀር  የ52 በመቶ እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል፡፡

እንደዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ገለጻ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ከብሄራዊ ባንክ የተላኩለትን አዳዲስ የብር ኖቶች በስሩ ለሚገኙት ሁሉም ቅርንጫፎች በፍጥነት በማዳረስ  ህብረተሰቡ ነባሩን የብር ኖት ያለምንም  ውጣ ውረድ በአዲሱ እንዲቀይርና የቁጠባ ሂሳብ በመክፈትም ገንዘቡን እንዲያስቀምጥ ማድረግ ችሏል ብለዋል ። ሁሉም የኤቲኤም ማሽኖቹም በአዲሱ የብር ኖት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲሱ የብር ለውጥ በገበያ ውስጥ ያለው የገንዘብ ዝውውር ህጋዊ የባንክ ስርዓትን እንዲከተል ከማገዙ በተጨማሪ ባንኮች የህብረተሰቡ የቁጠባ እና የባንክ አጠቃቀም ባህል እንዲዳብር በማስቻል ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ አድርጓቸዋል ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ።

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በገንዘብ ቅያሬው ላይ ትኩረት ሰጥቶ በሁሉም ቅርንጫፎቹ እያካሄደ በሚገኘው ጠንካራ እንቅስቃሴም  እስካሁን  1 ቢሊየን 785 ሚሊዮን 601 ሺህ ብር ነባር የብር ኖቶችን ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል።

በአፈጻፀም ረገድ የገንዘብ ለውጡ የባንኩን ደንበኞች ቁጥር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ 7 ነጥብ 7 በመቶ በላይ ማሳደግ ሲችል የቁጠባ ገንዘብ መጠኑንም ወደ 7 በመቶ ከፍ አድርጎታል ብለዋል። 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ መሰረት የጊዜ ገደቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ አዳዲስ የብር ኖቶችን የማሰራጨትና አሮጌዎቹን የማሰባሰብ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም ባለፉት ዓመታት በሃገሪቱ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ የቆየው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዘንድሮም  የተመሰረተበትን 11ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሃገርአቀፍ ደረጃ ይፋ ለተደረገው “የገበታ ለአገር” ፕሮጀክት የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ላለው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምና የትምህርት ግብዓቶች ማሟያ  የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም አቶ ሙሉጌታ ጨምረው ገልጸዋል።ባንኩ የሚያደርጋቸው መሰል ድጋፎች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መገለፁን ከባንኩ የተገኘ ዜና ጠቁሟል።

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ላለፉት 11 ዓመታት በመላው የሃገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 245 ቅርንጫፎቹ ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top