Connect with us

በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው
Photo: Social media

ዜና

በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

የጋዜጠኞችን ሙያዊ አቅም ለማሳደግ የልህቀት ማዕከል እንደሚገነባ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አስታወቀ።

የማዕከሉን ግንባታ ከሶስት እስከ ሶስት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ለማጠናቀቅ መታቀዱም ነው የተገለጸው።

በኢትዮጵያ 13 ዩኒቨርሲቲዎች የጋዜጠኝነት ትምህርት እንደሚሰጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም÷  የዩኒቨርሲቲዎቹ የጋዜጠኝነት ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይነት ያለውና አንዱ ከአንዱ እየገለበጠ እንደሚጠቀምበት ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጡ የተግባር ትምህርት ደካማ መሆን፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማት አለመሟላትና ትምህርቱ በብቁ ባለሙያዎች ባለመሰጠቱ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች የሙያ ክህሎት ችግር ያጋጥማቸዋል ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች የሚያጋጥማቸውን የአቅም ክፍተት ለመሙላት የሚረዳ የጋዜጠኝነት የልህቀት ማዕከል እንደሚገነባም አመልክተዋል።

ማዕከሉ ምሩቃን በሥራ ላይ ሆነው ሙያዊ አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት ድጋፍ እንደሚያገኙበት አቶ ወንድወሰን አስረድተዋል።

ባለስልጣኑ ማዕከሉ የሚቋቋምበትን ትልመ ሀሳብ(ፕሮፖዛል) ከኳታር መንግሥትና ከአልጄዚራ ብሮድካስት ማሰራጫ ጋር ባለፈው ዓመት ማዘጋጀቱንም ነው የገለጹት።

በትልመ ሀሳቡ ተጨማሪ ጉዳዮች ተካተው ዳግም  ተዘጋጅቶ መላኩንም አስታውቀዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱንና ሥራዎች በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄዱ ተጽዕኖ ማድረሱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው÷ ለማዕከሉ የሚያስፈልግ ቦታ በመለየት ላይ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ለማዕከሉ ግንባታ የሚያስፈልገው በጀት በኢትዮጵያና በኳታር መንግሥታት እንደሚሸፈን አመላክተዋል።

አቶ ወንድወሰን አያይዘውም ማዕከሉ የብሮድካስትና የሕትመት መገናኛ ብዙኃን የሚያስፈልጉት መሰረተ ልማት እንደሚኖሩትና የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠና ይሰጥበታል ብለዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top