Connect with us

ቤተ ክርስቲያን እሷ አስራት ሰብስባ ህዝቧን ለቄሳር የቄሳርን ስጥ ስትል ቄሳር ሀገር እንዲጠብቅ ነበር

ቤተ ክርስቲያን እሷ አስራት ሰብስባ ህዝቧን ለቄሳር የቄሳርን ስጥ ስትል ቄሳር ሀገር እንዲጠብቅ ነበር
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ቤተ ክርስቲያን እሷ አስራት ሰብስባ ህዝቧን ለቄሳር የቄሳርን ስጥ ስትል ቄሳር ሀገር እንዲጠብቅ ነበር

ቤተ ክርስቲያን እሷ አስራት ሰብስባ ህዝቧን ለቄሳር የቄሳርን ስጥ ስትል ቄሳር ሀገር እንዲጠብቅ ነበር፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደራጅና ራስህን፤ ፓትረያሪኩ ተደራጁና ቤተክርስቲያናችሁን ጠብቁ ያሉት ህዝብ

ከስናፍቅሽ አዲስ

እኛው ግብር ከፋይ እኛው ሰላም አስከባሪ ሁኑ መባል ቢያስቅም መራር እውነት ነው፡፡ ችግር ፈጣሪውን ፈልጎ እከሌ ነው ማለት ከችግር ሳይወጣ ሞትን እንደ ቀለብ ለሚሸምተው ህዝብ ትርጉም የለሽ ነው፡፡ 

አሁን ምክንያት እየተፈለገ ንጹህ ማረድ ቤተ ክርስቲያን ማቃጠል ፋሽን ሆኗል፡፡ ጉዳዮን እምነት ጋር ማያያዝ አይቻልም መጤም ተብለው ሰርተው መኖር ያቃታቸው የጉራጌና የስልጤ ሙስሊሞች የብዙ አካባቢ ጥቃት ሰለባዎች ናቸው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመተከል ተደጋጋሚ ግጭት ሳቢያ ለሟቾች ሀዘናቸውን ገልጸው ከዚህ በኋላ ህዝቡም ራሱን በማደራጀት ደህንነቱን መጠበቅና መከላከል እንዳለበት የሚገልጽ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ጫካ ውስጥ ያለ ህዝብ ሀገሬ ብሎ ከሚኖረው የእርሻ ስራ ትግል ባለፈ ብዙ ዓላማ ካነገበ አድፍጦ ተኳሽ ጋር በመታኮስ ራሱን ምን አድርጎ እንደሚከላከል ማወቅ ሌላ ሳይንስ ነው፡፡ ምክንያቱም የመተከል ተደጋጋሚ ወንጀል ተራ ግጭት ወይም ዘር ተኮር ጥቃት ብቻ ብለንው አናልፍም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራውን ቅድሚያ በለው በሚል ህጻናት የሚታረዱበት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የተደራጀ ተግባር መሆኑ ከተደጋጋሚነቱና መንግስት አደብ ሊያስገዛው ካለመቻሉ ተረድተናል፡፡

መተከልን የእኔ አደርጋለሁ የሚል ሃይል ቅድሚያ የኔ ናት ብሎ እንደ ሀገሩ ከሚኖርባት ህዝብ አጸዳለሁ በሚል ከተነሳ ያንን ደግሞ ሌላ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ከሚሹ የውጪ መንግስታት ጋር ካቀናጀው ደሃ ገበሬ ምን ይዞና በምን መልኩ ሰላሙን መጠበቅ ይችላል?

የፓትረያሪኩም መልእክት ተመሳሳይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን በገጠማት ተደጋጋሚ ችግር ሳቢያ የምታለቅስበት ማጣቱን የተረዱና ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ፡፡ ይኼ ሁሉ ሲሆን የሚደርስ አካል ቢኖር ኖሮ ያ ሁሉ ክርስቲያን በእርግጥም አይታረድም ነበር፡፡ 

ቤተ ክርስቲያን እሷ አስራት ሰብስባ ህዝቧን ለቄሳር የቄሳርን ስጥ ስትል ቄሳር ሀገር እንዲጠብቅ ነበር፡፡ ያን ስታጣ ልጆቿን ነቅታችሁ ተደራችጅታችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ብላለች፡፡

መንግስት አሁንም መንግስት ነኝ ብሎ በቁጭት መነሳት አለበት፤ ሰላም አድርጎ ያበልጽገን እንጂ ንዋይ እያየን አንለቅ፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top