Connect with us

“ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው”

"ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው"
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው”

“ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው”

(ውብሸት ሙላት ~ የሕግ ባለሙያ)

አንድ ቡድን የጦር መሣሪያ እንዲታጠቅ መፍቀድ እና ሌላውን ቡድን መከልከል፣ ታጣቂውን ቡድን በማገዝ መሣሪያ እንዳይታጠቅ የተከለከለውን ቡድን ማጥቃት ነው የሚሆነው። እኩል መሣሪያ መታጠቅ መከባበርን ካልሆነም መፈራራትን ያመጣል። 

እብሪተኛ ታጣቂ፣ ሸማቂና በጥላቻ የሰከሩ ሴረኛ ቡድኖች ዘው ብለው ባሻቸው ጊዜ መሣሪያ የሌለውን ሰላማዊ ሰው ለመግደል አይሮጥም። መገደልም እንዳለ ቆም ብሎ ያስባል። መተክል ውስጥ በታጣቂዎች እየተገደለ ያለው አማራ እና አገው ፣ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም፣ ባለመታጠቁም ጭምር ነው። 

መተከልን የለየለት የግጭት  ቀጠና እና የሞት ምድር ለማድረግ ሌት ተቀን በተቀናጀ መንገድ ከሚሠሩ ቡድኖች መካከል ኦነግ ሸኔና ትህነግ ዋናዎቹ ናቸው። ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ የማልፈልጋቸው (መግለጽ አስፈላጊ ባለመሆኑ!) ሌሎች ኃይሎች መኖራቸውን በመዘንጋት አይደለም፤ በተለይ ደግሞ ለጥቃት ፈጻሚዎች (ለገዳይ ታጣቂ ቡድኖች) ከለላ የሚሰጡ አካላት።

ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ስለ ራስን መከላከል የተናገሩትን “ስህተት ነው” በማለት የተለያዩ ምክንያቶችን በመደረት ያላማቋረጥ በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዘመቻ የከፈቱት የኦነግ-ሸኔ እና የትህነግ ሰዎች መሆናቸውን ላጤነ ሰው መልእክቱ ግልጽ ነው።  ዘመቻው ከደረጀ ደገፋ ቱሉ እስከ ትግራይ ቴሌቪዥን (ከፊንፊኔ እስከ መቐሌ) ነው። 

በየዕለቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደለው አማራና አገው ለእነሱ ግዳያቸው ነው።  እየተገደለ ያለው ወገን ራሱን መከላከሉ ደግሞ ለጥምር ዘመቻቸው ሳንካና ስጋት መሆኑ ነው። ታጥቆ የሚኖረውን ሌላውን ሕዝብ መሣሪያ እንዲፈታ የሚል እንኳን ከጽሑፋቸውም ከንግግራቸውም ውስጥ የለም። ያንገበገባቸው እንዴት ዕለት ዕለት በዘግናኝና አሰቃቂ ሁኔታ እየተገደለ ያለው አማራ ራሱን ይከላከል ይባላል የሚለው ነው። 

ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው!!!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top