Connect with us

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ በ 20 ቀበሌዎች የሚገኝ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ወደመ

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ በ 20 ቀበሌዎች የሚገኝ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ሙሉ ለሙሉ ወደመ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ኢኮኖሚ

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ በ 20 ቀበሌዎች የሚገኝ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ወደመ

በአማራ ክልል ባቲ ወረዳ በ 20 ቀበሌዎች የሚገኝ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ሙሉ ለሙሉ ወደመ

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ከተከሰተባቸው 22 ቀበሌዎች ውስጥ በ20 ቀበሌዎች የተዘራው የሰብል ምርት ሙሉ ለሙሉ መውደሙን የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የአንበጣ መንጋው በአካባቢው መከሰት የጀመረው ከመስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

የአንበጣ መንጋው ከሰብል በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙ ለከብቶች መኖ የሚውሉ ተክሎች ላይም ጥቃት እያደረሰ በመሆኑ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን በስፍራው  የሚገኘው  የኢቢሲ ሪፖርተር ታዝቧል።

የወረዳው አርሶ አደሮች “ሰብላችን ወድሞብናል አሁን ደግሞ የአንበጣው መንጋ የእንሰሳቶቻችንን መኖ እንዳያጠፋብን ስጋት ዉስጥ ነን” ብለዋል።

በአካባቢ በአብዛኛው የተዘራው የማሽላ ምርት ሲሆን የአንበጣ መንጋው የማሽላ እሸቱን በልቶ አውድሟል።

የአንበጣ መንጋው ከባቲ ወረዳ ባሻገር በደቡብ ወሎ ወረባቦ ወረዳ እና ሌሎች አካባቢዎችም ላይ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በባህላዊ እና በዘመናዊ መንገድ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የመንጋው ብዛት ከፍተኛ በመሆኑ ውጤት ለማምጣት አለማቸሉን የባቲ ወረዳ  አስታውቋል።

በፌዴራል መንግሥት በኩል በጄት የኬሚካል ርጭት ለማድረግ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ጥረቱ በቂ እንዳልበርም ተገልጿል።

በሌላ በኩል  በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 21 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ በድሬዳዋ በ22 ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በ10 ሺህ ሔክታር ሰብል እና ግጦሽ ላይ ጉዳት ማድረሱን የአስተዳደሩ የግብርና፣ ውኃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ አስታውቋል።

በድሬደዋ ከተማ በአንበጣው መንጋው ጉዳት ከደረሰባቸው የእህል ዘሮች የአተር ሰብል እና የቲማትም እና የፍራፍሬ ተክሎች ይገኙበታል።

አንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ጭስ በማጨስ እና ድምፅ በማሰማት እንዲሁም በኬሚካል ርጭት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከአቅም በላይ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የበረሃ አንበጣው ቀሪ ሰበሎችን ከማውደሙ በፊት ለመከላከል የመከላከያና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሌሎችን አጋር አካላት በማሳተፍ የደረሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

ግብርና ሚኒስቴር የአንበጣ መንጋን ለመከላከል እስከ ፊታችን ረቡዕ ድረስ ኬሚካል የሚረጩ 5 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ከውጪ ለማስገባት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል። (EBC)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top