Connect with us

ለቀድሞ መምህራን የተላለፈ አገራዊ ጥሪ

ለቀድሞ መምህራን የተላለፈ አገራዊ ጥሪ
Ministry of Education Ethiopia

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ለቀድሞ መምህራን የተላለፈ አገራዊ ጥሪ

ለቀድሞ መምህራን የተላለፈ አገራዊ ጥሪ

በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያዎች ሀጋራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ7 ወራት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ  ከዚህ ቀደም  በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ መምህራን  በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማገልገል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርትን በሚያስቀጥልበት ወቅት  በትምህርት ቤቶች አካላዊ እርቀትን ለማስጠበቅ የተማሪዎች ቁጥር ከ20-25 እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደየ አካባቢያቸው ሁኔታ  በፈረቃ ትምህርት የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በዚህም ወቅት በትምህርት ቤቶች የመምህራን እጥረት እንዳይኖር ለማድረግ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና የ መምህርነት ስልጠናን ወሰደው ሌላ ዘርፍ የተቀላቀሉ ባለሙያዎች  በየአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) “እኔም አስተምራለሁ” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች  ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በ መምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በዚህም መሰረት ባለሙያዎች በአቅራቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሄድ እና በመመዝገብ የትምህርቱን ዘርፍ በሙያቸው እንዲያግዙ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

(የትምህርት ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top