Connect with us

በሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

የተዘጉ የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ሥራ ሊመለሱ ነው
የማዕድንና ነዳጅ ሚ/ር

ኢኮኖሚ

በሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

በሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የሶስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ሚኒስትርሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡

ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡

በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ለማቅረብ ነበር፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል የተደረገው የወርቅ ማሻሻያ ዋጋ  የወርቅ አቅራቢዎችን በመሳቡ ምክንያት ከታቀደው በ298 ነጥብ 9 በላይ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል።ከዚህም ከ178 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በተጨማሪም ባለፉት ሶስት ወራት የተቋሙ የ10 አመት እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚመለከታቸው አካላትም ተልኳል።

የማአድንና ነዳጅ ዘርፉ የፖሊሲ ማሻሻያም ተደርጎበታል ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።

በሀገሪቷ የሌለውን የወርቅ ቤተ ሙከራ ለማቋቋም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በማእድንም ይሁን በነዳጅ ዘርፍ ላይ ላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን የህግና ተግባራዊ ማሻሻያዎች እየተሰሩ መሆኑን ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

 ቀጣይ ጊዜያትም የተጀመሩ የሰነድ ስራዎች የሚጠናቀቁበትና ተቋማዊ ግንባታው ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ይሆናል ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።

(የማዕድንና ነዳጅ ሚ/ር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top