Connect with us

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ንጹሃን ሰዎች ተገደሉ

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ንጹሃን ሰዎች ተገደሉ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

ዜና

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ንጹሃን ሰዎች ተገደሉ

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ንጹሃን ሰዎች ተገደሉ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት፣ ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም)በማንዱራ ወረዳ ድኋንዝ ባጉና ቀበሌ ትናንት ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት የ 12 ሰዎች ህይወት ማለፉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ገልጸዋል።

ከሟቾቹ በተጨማሪ አንድ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ደረሶበት የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

ሶስት ሰዎች የአንድን ግለሰብ መሳሪያ ነጥቀው በመሰወራቸው ምክንያት በአካባቢው የሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ሃላፊው አስታውቀዋል።

በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ የሆነ እና መሳሪያ የተነጠቀበት ግለሰብ ቤተሰቦች በፈጸሙት ድርጊት አማካኝነት የሰዎች ህይወት እንዳለፈ ገልጸው አጥፊዎችን በህግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አቶ ጋሹ ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ መሳሪያ ነጥቀው የተሰወሩ ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች እስካሁን ያልተያዙ ግለሰቦችን ወደ ህግ ለማቅረብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ የጸጥታ አካላት እየሰሩም እንደሆነ ተጠቁሟል።

የተከሰተው ድርጊት በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም እንኳን ከጀርባ ተልዕኮ ያላቸው ሃይሎች መኖር አለመኖራቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በቀጠናው በተደጋጋሚ ግጭቶች ሲስተዋሉ እንደቆዪ ቢታወቅም ትናንት የተከሰተው የሰዎች ሞት ግን ብሄርን መሰረት ያደረገ እንዳልሆነም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው በሁሉም የጸጥታ አስከባሪዎች አማካኝነት የማረጋጋት ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ህብረተሰቡ ባለበት ተረጋግቶ የዕለት ተዕለት ስራውን እንዲሰራም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቀጠናውን በዘላቂነት በማረጋጋት እና የህግ የበላይነትን በማስፈን የህዝቦችን ሰላም ለማረጋገጥ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ይታወቃል።

(የመተከል ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top