Connect with us

ኢዜማ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርን ከሰሰ

ኢዜማ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርን ከሰሰ

ዜና

ኢዜማ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርን ከሰሰ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ነሃሴ 25 /2012 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤት ልቡ ለፈቀደው ሰው እያደለነው። የመሬት ወረራውም በመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀር በመታገዝ ወረራው በከተማዋ እየስፋፋ መሆኑን ደርሼበታለሁ ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ይህ ኢዜማ አጠናሁት ያለው የጥናት ውጤት አስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ተቀምጠን እንወያይበት ብለው ከኢዜማ አመራሮች ጋር ከተወያዩ በኋላ በህገወጥ መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤት ያደሉ እና የመሬት ወረራ ያካሄዱ አካላት ካሉም አጣርተው በህግ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተናግረው እንደነበር ኢዜማ አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የከተማ አስተዳደሩ ህገወጥ ድርጊት በፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ የመውሰድም ሆነ አሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ ያለውን የመሬት ወረራ ለማስቆም ፍላጎት የለውም ሲል ወቅሷል ኢዜማ ።

በመሆኑም ኢዜማ የዚህን መፍትሄ ለመጠቆም መሬታችንን ተነጥቅን ከሚሉ አርሶ አደሮች እና ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት መስከረም 15 /2013 ዓ/ም ቀጠሮ አስናድቶ ሲጠብቅ የከተማ አስተዳደሩ በወቅቱ ከነበረው አመታዊ ክብረ በአል ጋር በተያያዘ በስራ መደራረብ ምክንያት እንዳልቻሉ አሳውቀው ውይይቱ መሰረዙን ኢዜማ ተናግሯል።

ከዚያ በኋላ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ/ም በራሱ በኢዜማ ጽሕፈት ለመስብሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጸሕፈት ቤት ውይይት ማድረግ አትችሉም ሲል አግዶናል ብሏል ፓርቲው ።

የከተማ አስተዳደሩ ከንትባ ጽሕፈት ቤት ይህንን ደብዳቤ በግልባጭ ያሳወቀው ለኢትዮጵያ መረጃ እና ደህንነት ፣ ለፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን ጠቅሶ ይህ አካሄድ የሚጠቁመው ከለውጡ ወዲህ እነዚህ የተጠቀሱት ተቋማት የህዝብ አገልጋይ እንደሆኑ እየተገለጸ ባለበት ወቅት የከተማ አስተዳደሩ የግል አላማ እና ፍላጎት ማስፈጸሚያ እንዲውል የጠየቀበት አግባብ ልክ አለመሆኑን ጠቁሟል ኢዜማ ።

ፓርቲው እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገ መንግስቱ የተሰጠኝን የመሰብሰብ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቴን በመገደቡ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቻለሁ ብሏል ።

የክሱ ፍሬ ሃሳቡም በህገ መንግስቱ የተቀመጡት የመሰብሰብ እና ሃስብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዳይገደብ እና እስካሁንም እንዳልወያይ የተከለከልኩት አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ ሲል ዳኝነት የሚጠይቅ መሆኑን ነው ኢዜማ ያስታወቀው።

ኢዜማ እንዳለው መንግስት አሁን እየሄደበት ያለው መንገድ ወደ ዱሮው የአፈና ስርዓት ለመመለስ መሆኑን ያመላክታል ፣ ይህ ሁላችንንም አይጠቅምም ሲል አበክሮ አሳስቧል ።

የመሬት ወረራ እና የህገወጥ የጋራ መኖሪያ እደላን አስመልክቶ ለፌደራል የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ለፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እና ሌሎች ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጉዳዩን እንዲያጣሩ ያመለክትን ቢሆንም ተቋማቱ እስካሁን የሰጡት ምላሽ የለም ሲልም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ዛሬ ለጋዜጦች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።(ኢሳት)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top