Connect with us

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ መልዕክት

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ፒ ኤች ዲ) መልዕክት
Photo: Social media

ዜና

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ መልዕክት

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ መልዕክት

ሸክላ_ድስት!…

“በሸክላ  ድስት የሚዘጋጅ  ሽሮም ሆነ ዶሮ ወጥ ከብረት ድስት በተለየ መጣፈጥ የቻለበትን ሚስጥር መረዳት መልካም ነው ፡፡ በቀዳሚነት ሸክላው ከብረት ድስት በተለየ እርጋታን የተላበሰ መብሰያ ሙቀት የማቀበል ባሕሪው ተጠቃሽ ነው ፡፡ ሸክላ ድስት ሁሉም የወጥ ማጣፈጫ ግብዓቶች በውስጣቸው ያኖሩትን መልካም መዓዛ እንዲሰጡ አያጣድፍም አያንገበግብም ፡፡ ይልቁንም ተፈጥሯዊ ምቹ ከባቢን ይፈጥርላቸዋል ፡፡ 

ሸክላ ድስት በውስጡ የተበታተኑና እዚያና እዚህ የተረጩ ሁሉም ማጣፈጫ መዓዛዎች እንዲወጡ ብቻ ሳይሆን በሚዛናዊነት ወደማዕከል የሚመጡበትንና ጣፋጭ ውሁድ የሚፈጥሩበትን ድንቅ ብልሃት ጭምር የተላበሰ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂያዊ ቁስ ነው ፡፡ 

አዲሱ የሀገር ግንባታ ፕሮጀክታችን ይበልጥ የሠመረ እንዲሆን ወደውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ በመመልከት እርጋታን ፣ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ ምቹ ከባቢ መፍጠርን እና መደመርን መሠረት ያደረገ የመካከል መንገድ የመከተልን ድንቅ ሂደት ከሀገር በቀሉ ቴክኖሎጂ ፣ ከሸክላ ድስት መቅሰም ይኖርበታል፡፡”

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top