Connect with us

አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮሮና ሕመም አያገግሙም?

አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮሮና ሕመም አያገግሙም?
Photo: Social media

ጤና

አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮሮና ሕመም አያገግሙም?

ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ።

አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል።ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም።

ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል?

በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ።

በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል።

ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች።

ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል።

በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል።

ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል።

ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም።

ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም።

ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል።

ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ።

ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል።

የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም።

ህመሙ የተለመደ ነው?

በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው።

ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል።

እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ።

“ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ።

ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል?

ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም።

ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ።

ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ።

በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል።

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ።

ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል።አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው።በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።(BBC)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top