Connect with us

ከአስር ሰዎች አንዱ በኮሮና ቫይረስ ሊያዝ ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት

ከአስር ሰዎች አንዱ በኮሮና ቫይረስ ሊያዝ ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

ከአስር ሰዎች አንዱ በኮሮና ቫይረስ ሊያዝ ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት

በግምት ከ 10 ሰዎች መካከል አንዱ በኮሮናቫይረስ ሊያዝ ይችላል፣ በዚህም አብዛኛው የዓለም ህዝብ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጋላጭ ይሆናል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ባለሙያ የሆኑት ማይክ ራያን በኤጀንሲው ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ላይ እንደተናገሩት በደቡብ ምስራቅ እስያ አንዳንድ አካባቢዎች ወረርሽኙ እየጨመረ መሆኑንና በአውሮፓ እና በምስራቅ ሜድትራንያን አካባቢዎች ደግሞ የወረርሽኙ እና የሞት መጠን እየጨመረ መጥቷል፡፡

ከሀገር ሀገር፣ ከከተማ  ገጠር  እንዲሁም እንደ ማህበረሰቡ ቢለያይም አሁን ያሉን ግምቶች ከጠቅላላው የዓለም ህዝብ ቁጥር 10 በመቶው በኮሮና ቫይረስ ሊያዝ ይችላል ብለዋል ራያን፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን መነሻ ለማጣራት ወደ ቻይና የሚሄዱ የባለሙያዎችን ዝርዝር ማቅረቡን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል ፡፡

አሜሪካ ለዓለም የጤና ድርጅት የምትከፍለውን 80 ሚሊዮን ዶላር እንደማትከፍል ይልቁንም ወደ ተባበሩት መንግስታት ሂሳብ እንደሚዛወር መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡(EBC)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top