Connect with us

ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ዝናብ በያዝነው ሳምንትም ይቀጥላል አለ

ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ዝናብ በያዝነው ሳምንትም ይቀጥላል አለ

ዜና

ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ዝናብ በያዝነው ሳምንትም ይቀጥላል አለ

በቀጣዮቹ ሰባት ቀናት በምስራቅ አፍሪካ የዝናቡ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የምስራቅ አፍሪካ የልማት የበየነ መንግስታትድርጅት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡

ከመስከረም 26 ቀን ጀምሮ በሚኖሩት ሰባት ቀናት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከ50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር መካከለኛ ዝናብ እንደሚጠበቅ ድርጅት አስታውቋል፡፡

በደቡባዊ ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር መካከለኛ ዝናብ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም በምዕራብ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ደቡብ ሱዳን፣ በምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ በምዕራብ የቡሩንዲ ክፍሎች፣ የሰሜን ምዕራብ ታንዛኒያ፣ የመካከለኛው እና የምዕራብ ኬንያ ክፍሎች እንዲሁም በማዕከላዊና ደቡብ ሶማሊያ የተጠናከረ ዝናብ እንደሚጠበቅ መረጃው አመልክቷል፡፡

በእነዚህ ቀናቶች ከመካከለኛው እስከ ደቡባዊ የሱዳን አካባቢዎች ከ50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይጠበቃል፡፡

የሰሜን እና የደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን ክፍሎች፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኤርትራ፣ ሰሜናዊ እና ደቡብ ሶማሊያ፣ ምስራቅ, ማዕከላዊ እና ሰሜን-ምዕራብ ኬንያ፣ እና የባህር ዳርቻዎች እንዲሁም ምዕራባዊ ታንዛኒያ በዚሁ መጠን ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በሰሜን ሱዳን፣ በጅቡቲ፣ በሰሜን እና በደቡባዊ ኤርትራ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በሰሜን ሶማሊያ አንዳንድ ክፍሎች ፣ በጅቡቲ ፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ ኬንያ አንዳንድ ክፍሎች እና በብዙ ማዕከላዊ ታንዛኒያ ክፍሎች ደረቅ ሁኔታዎች እንደሚጠበቁም ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡(FBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top