Connect with us

በግብጽ በረሃዎች የዓለም ትልቁን የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም እየተሰራ ነው

በግብጽ በረሃዎች የዓለም ትልቁን የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም እየተሰራ ነው
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

በግብጽ በረሃዎች የዓለም ትልቁን የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም እየተሰራ ነው

ዜድ ፒ ኢ ኤስ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በግብጽ ሚኒያ ግዛት በስተምዕራብ በኩል በዓለም ትልቁን የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ለማቋቋም እየሠራ ነው፡፡

በግብጽ እና በተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ የጋራ ሀብት የሆነው ፕሮጀክቱ በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚሠራ ነው፡፡
እስካሁንም በግዛቱ 300 ጥልቅ የውኃ ጉድጎዶችን ለመቆፈር ካላቸው እቅድ 120 የሚሆኑትን አሳክተዋል፡፡

በግብጽ የዚድ ፒ ኢ ኤስ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ሊ ዌይ ከ2016 (እ.አ.አ) ጀምሮ ቻይናውያን ከፍተኛ ባለሙያዎች የግብጽ ባለሙያዎችን በዘርፉ እያሰለጠኑ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በጥልቅ የጉድጎድ ውኃ ቁፋሮ አማካኝነት የግብጽ በረሃዎችን ወደአረንጓዴ ልማት የሚመልስ ትልቅ ሥራ ነውም ብለዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ይህ ፕሮጀክት የቻይና “የቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሺቲቭ” የትብብር አካል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ76 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማልማት የሚችል ሲሆን በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ 21 ሺህ ሄክታር የሚሆነው መሬት ያለማል ብለው እንደሚጠብቁ ዥንዋ እና ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግበዋል፡፡

ግብጽ ከዚህ ቀደም ዓባይ ውኃ ብቸና የውኃ ምንጯ እንደሆነ በመግለጽ ስትከራከር ነበር፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ግብጽ ከፍተኛ የከርሰ ምድር ውኃ ባለቤት እንደሆነች በመግለጽ ትሞግታለች፡፡ ይህ የስኳር ልማት ፕሮጀክትም የኢትዮጵያን የመከራከሪያ ጭብጥ ተገቢነት የሚያመላክትና የግብጽ በረሃዎች ጭምር እጅግ ከፍተኛ የውኃ ተጠቃሚ የሆነ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ለማቋቋም የሚያስችል የውኃ ክምችት ስለመያዛቸው ማሳያ ነው፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top