Connect with us

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ኮሚቴው ትምህርት ቤቶችን ገምግሞ ውሳኔ ሲያሳልፍ መሆኑ ተገለጸ

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ኮሚቴው ትምህርት ቤቶችን ገምግሞ ውሳኔ ሲያሳልፍ መሆኑ ተገለጸ
Photo: Social media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ኮሚቴው ትምህርት ቤቶችን ገምግሞ ውሳኔ ሲያሳልፍ መሆኑ ተገለጸ

ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ ለመክፈት ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ያሳለፈው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣው ኮሚቴ ዝግጁነታቸውን ሲያረጋግጥ ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ለትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ይሁንታ የሚሰጠው ኮሚቴ በአብላጫው ወላጆች የሚሳተፉበት ሆኖ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከአስተዳደር ዘርፍና ከወላጆች የተውጣጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትምህርትን ለማስጀመር ከቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አንዱ ይህንን ኮሚቴ ማዋቀር ሲሆን፣ የተዋቀረው ኮሚቴ በመጪዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝን ተከላክሎ ለማስተማር የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆናቸውን፣ ከሚኒስቴሩ የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን፣ በየትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዓት መሟላቱን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ትምህርቱን ማስኬድ ይችላሉ ወይ የሚለውን ይገመግማል ተብሏል፡፡

ኮሚቴው ትምህርት ቤቶችን ገምግሞ ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በግል ትምህርት ቤቶች የወላጅ ኮሚቴዎች የየትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ካላረጋገጡና ወረርሽኙን ተከላክሎ ለማስተማር የሚያስችል ሁኔታ አለ ብለው ካላመኑ፣ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመር እንደማይችሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ፣ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ክፍያ ላይ ምንም ጭማሪ እንዳያደርጉ ያስቀመጠውን ውሳኔ የተላለፉ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን ለጊዜው ማገዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በአንድነት ኢንተርናሽናልና በግሪክ ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤቶች ላይ የተላለፈው ጊዜያዊ ዕገዳ፣  የወላጅ ኮሚቴዎች በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመርያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ሪፖርት እስኪያቀርቡ ድረስ፣ ምንም ዓይነት የትምህርት ሥራ እንዳያከናውኑ መታገዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡(ምሕረት ሞገስ ~ ሪፖርተር)

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top