Connect with us

“ጠላትን የመመከት አስተማማኝ ብቃት አለን” የኢት. አየር ኃይል

"ጠላትን የመመከት አስተማማኝ ብቃት አለን" የኢት. አየር ኃይል
Photo: Social media

ዜና

“ጠላትን የመመከት አስተማማኝ ብቃት አለን” የኢት. አየር ኃይል

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ሊያጋጥም የሚችል የትኛውም የጠላት እንቅስቃሴ መከላከል የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነት እንዳለው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታወቀ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ ብቃት ባላቸው አባላትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።

ቀደም ሲል የአጭር ጊዜ በረራ ብቻ ያደርጉ የነበሩት ተዋጊ አውሮፕላኖች አሁን ከአራት ሰዓት በላይ መብረር የሚችሉና ዲጂታል መሆናቸውን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ የአየር ክልል በመጠበቅ ሂደት በአንድ ማዕከል በመሆን መቆጣጠር፣ ትእዛዝ መስጠትና ግዳጆች በፍጥነትና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲፈፀም ማድረግ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱንም ሜጀር ጄኔራል ይልማ ገልጸዋል።

ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በተለይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከየትኛውም ጥቃት መጠበቅ የአየር ሃይላችን ዋነኛ ተልእኮ መሆኑን በአግባቡ እንገነዘባለን ብለዋል።

በግድቡ ዙሪያ የማይቋረጥ የአየር ሃይሉ ዋነኛ ክትትልና ጥበቃ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በዚህ ዙሪያ ማንኛውንም ትንኮሳም ይሁን የጠላት እንቅስቃሴ የመመከትና የማስቀረት አስተማማኝ ብቃት አለን ነው ያሉት።

ቀድሞም ስመ ገናናነቱ የሚወሳው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተልእኮውን በማሳካት፣ በጀግንነትና ውጤታማነቱ የሚታወቅ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አሁን ለደረሰበት ያለፈው ዋነኛ መሰረቱ መሆኑን የገለጹት ሜጀር ጀነራል ይልማ አሁን ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቀ፣ በአጭር ጊዜም በብቃት ተልእኮ የመፈፀም ብቃት አለው ብለዋል።

አየር ሃይል አሁን ላይ በአቪየሽንና በአየር መከላከያ ዘመኑ የተደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ላይ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የባለሙያዎች ስልጠና በዘመናዊ የምስለ በረራ ስልጠና የታገዘ እና ስልጠናውም ይሁን ተዋጊ አውሮፕላኖች ከአናሎግ ወደ ዲጂታል መቀየሩንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአገሪቱን የአየር ክልል በመቆጣጠርና ተልዕኮዎች እንዲፈፀሙ ለማድረግ በአንድ ማእከል በመሆን ትእዛዝ መስጠትና መከታተል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል በቀድሞው አጠራር ከታ ሜዳ አሁን ደግሞ ሀረር ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1936 ዓ.ም እንደተመሰረተ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ስዊዲናዊው ካውንት ቮሮንስ ሲሆኑ ከእርሳቸው በኋላ በ1953 ዓ.ም ኢትዮጵያዊው ጄኔራል አሰፋ አያና መሪነቱን ተረክበው በኢትዮጵያዊያን ቅብብሎሽ እየተመራ 77 ዓመታትን አስቆጥሯል ።(ኢኘድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top