Connect with us

ፅዳት ~ በመስቀል አደባባይ

ፅዳት ~ በመስቀል አደባባይ
Photo: Social media

ዜና

ፅዳት ~ በመስቀል አደባባይ

የደመራ ክብረ በአል የማክበሪያ ስፍራ በአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት ዛሬ ጠዋት ተጸድቷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለደመራ በአል ማክበሪያ ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ ቃል በገባው መሠረት በተባለው ጊዜ ዝግጁ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ በጽዳት ዘመቻው ላይ የተሳተፉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ገልጸዋል፡፡

የደመራ ክብረ በዓል የከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በውስን የእምነቱ ተከታዮች ተሳታፊነት የሚከበር ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለመስቀል ደመራ እንዲደርስ ርብርብ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምዕመናኑም የደመራ በአልን ሲያከብር እራሱን ከኮቪድ 19 በመጠበቅ መሆን እንዳለበትም አቶ ኤፍሬም በጽዳት ዘመቻው ወቅት ተናግረዋል፡፡

የደመራ ክብረ በዓል የማክበሪያ ቦታውን የጸረ-ተህዋስ ኬሚካል ርጭት በማድረግ የማጽዳት መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡

የደመራ ክብረ በዓል የማክበሪያ ስፍራ የጽዳት ዘመቻ ላይ የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከሁሉም ሀይማኖቶች የተውጣጡ ወጣቶች ፣ የጽዳት ሰራተኞች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

(የአ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top