Connect with us

በክረምቱ ዝናብ የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ313 ሺህ በላይ ደረሰ

ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ዝናብ በያዝነው ሳምንትም ይቀጥላል አለ
Photo: Social Media

ዜና

በክረምቱ ዝናብ የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ313 ሺህ በላይ ደረሰ

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ዳሮታ በሰጡት መግለጫ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ለወንዞችና ተፋሰሶች ከአቅም በላይ መሙላት ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ወንዞቹ በአቅራቢያ ወደሚገኙ አካባቢዎች በመፍሰሳቸው ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑን ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም ተጠናክሮ በቀጠለው ከፍተኛ የዝናብ መጠን ሳቢያ በደረሰው መጥለቅለቅ ከ313 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤትና ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል።

በአምስት ክልሎች በተከሰተ መጥለቅለቅም ከ1 ሚሊዮን 95 ሺህ የሚልቁ ዜጎችም በተለያየ መጠን የሚገለፅ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ።

ከ መተሃራ እስከ ጅቡቲ ድንበር በሚዘልቅ ስፍራ አፋር 16 ወረዳዎችን ያጥለቀለቀው የአዋሽ ወንዝ ሙላት 144 ሺህ ዜጎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል።

በክልሉ የደረሰው ጉዳትም ቀድሞ ከተተነበየው በ3 እጥፍ ጭማሪ እንዳለው ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ይፋ አድርገዋል።

ከአፋር ውጭም በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል 27 ሺህ ፤ በጋምቤላ ከ18 ሺህ በላይ ፤ በኦሮሚያ 46 ሺህ ፤ እንዲሁም በአማራ ክልል ከ10ሺህ በላይ ዜጎች ባጋጠማቸው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

አደጋው ስፋት ያለውና ከባድ ቢሆንም እስካሁን የአንድም ሰው ህይወት አለማለፉን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

የተፈናቀሉና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችን አፋጣኝ ርዳታ እንዲያገኙና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ድርጅቶችና ዜጎች የተጎዱትን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙም ጥሪ ቀርቧል።(አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top