Connect with us

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆኑ

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆኑ
Photo: Social Media

ዜና

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆኑ

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆኑ
—-
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኖርዌይ የሚዘጋጀውን የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዘንሮውን ሽልማት በማሸነፋቸው ከአራት ቀናት በኋላ መስከረም 12 2013 ዓ.ም በኦስሎ በሚዘጋጅ ስነ-ስርዓት ይቀበላሉ ተብሏል፡፡

የአዋርዱ አሸናፊ በመሆኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአለምን መሰረት ነቀነቀ እንጂ መሰረቷን አልሰበራትም ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፡፡ ወረርሽኙ ለዓለም ጠንካራ ቁም ነገር አዘል ትምህርት ጥሎ ማለፉንም ጠቁመዋል፡፡

ታሪካዊውን ዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ፈተና ለመከላከል አሁንም ተባብሮ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ሸልማቱ የአጋርነት እና የትብብር ውጤት ማሳያ ምልክት ነውም ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ባጋጠመው ፈታኝ ወቅት ላይ የኖርዌይ መንግስት ለሰጠው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ #ebc

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top