Connect with us

በመለያየትና በበላይነት ጎዳና የተገኘ ትርፍ የለም!

በመለያየትና በበላይነት ጎዳና የተገኘ ትርፍ የለም!

ነፃ ሃሳብ

በመለያየትና በበላይነት ጎዳና የተገኘ ትርፍ የለም!

በመለያየትና በበላይነት ጎዳና የተገኘ ትርፍ የለም!
(ሙፈሪያት ካሚል)

የበላይነትና የመለያየት ጎዳና ተጫጭኖት የቆየው አለም ይህ ጉዞ መቋጫው አደገኛ ገደል መሆኑ ግልፅ እየሆነ መጥቷል፡፡ እንኳን የኢትዮጵያውያን የሰው ዘሮች እድል ፈንታ ከመደጋገፍና አንድነት ውጪ አደጋ ውስጥ መውደቁን ፤ከክስተቶቹ መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡

ይህ ጎዳና ካደረሳቸው ጉዳቶችና ከጥፋቶች ጭስ እና ከፍርስራሾቹ ስር አዲስ የአንድነትና የአጋርነት መንገድ ብቅ ማለት ጀምሮ ነበር ፡፡ ምንም እንኳን የኋልዮሽ ትንቅንቅ ቢገዳደረውም። ይህ መንገድ ዳግም አለማችንን እና ህዝቦቿን በዚህች ብርቅዬ ፕላኔት ውስጥ እንደ አንድ የህይወት ቤተሰብ መመልከት የጀመረ መንገድ ነው፡፡

ህልውናችን የተሳሰረ ፤አንዱ በአንዱ ላይ የተመረኮዘ፤ ያልተነጣጠለና የጋራ ፍላጎትና ክብር ፤በመደጋገፍ መስራት አለማችንንና ህዝቦቿን የምንታደግበት መንገድ ነው፡፡

የእንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ውጤት አጋርነት ነው፤ መጓጓዣው መከባበር ነው፤ መጨረሻው ደግሞ ሰላም ነው፡፡ ይህ እይታ ህይወትን ከነሙሉ የብዝሃነት ሀብቱ ይቀበላል፤ ለእኛም ማለቂያ የሌለው የፈጠራ ዑደት፣ ነጻነትና ተስፋን ይሰጠናል፡፡

የመለያየት መንገድ ደግሞ ልዩነቶቻችንን የተወሰኑ ክፍሎች ከሌላው የተሻሉ፣ የበለጠ ዋጋ ያላቸውና፣ ሁሉ የሚገባቸው ናቸው የሚለውን እምነት ለመደገፍ ይጠቀምባቸዋል፡፡ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ውጤት የበላይነት ነው፤ መጓጓዣው ጉልበት ነው፤ መጨረሻው ደግሞ ጥፋት ነው፡፡ ይህ እይታ ህይወትን ያቀጭጫል፣ እኛንም በማያቋርጥ የጸብ፣ የጭቆናና የትግል ዑደት ውስጥ ይከተናል፡፡

ይህ እንግዲህ እያንዳንዳችን በየራሳችን ህይወት ውስጥና ህይወታችንን በምንመራበት አኳኋን ላይ ልንመርጠው የሚገባ ምርጫ ነው፡፡ የአንድነትንና የአጋርነትን መንገድ የምንመርጥ ሰዎች የአዲስ ነገ ጀማሪዎች ነን፡፡ አሮጌው ዓለም በዙሪያችን በሚፈራርስበት ጊዜ አዲስ ዓለም እየገነባን ነው ማለት ነው…ይቀጥላል

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top