Connect with us

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ህወሓት ማሸነፉ ተገለፀ

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ህወሓት ማሸነፉ ተገለፀ
Photo: BBC

ዜና

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ህወሓት ማሸነፉ ተገለፀ

የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም በተለይ ለቢቢሲ እንደገለፁት ህወሓት ከአጠቃላይ የመራጮች ድምጽ 98.2 በመቶ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል።

በዚህም የተነሳ የክልሉ ምክር ቤት ካለው 190 ውስጥ 152ቱ በህወሓት የሚያዝ ሲሆን 38ቱ ደግሞ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።

ህወሓት የምክር ቤቱን መቀመጫ 80 በመቶ ሲይዝ በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት ባደረገው የውክልና ማሻሻያ ውሳኔ መሰረት ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የምክር ቤቱ ምርጫ በምርጫ ተፎካካሪ ለነበሩ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።

በምርጫው ባይቶና፣ ትግራይ ነጻነት፣ ሳልሳይ ወያነ እንዲሁም አሲምባ እንደ ቅደም ተከተላቸው ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል።
ፓርቲዎቹ በቅደም ተከተል ያገኙት ድምፅ፦

• ህወሓት፡ 2, 590, 620 (98.2 %)
• ዓባይ ትግራይ፡ 20, 839 (0.8%)
• ትግራይ ነጻነት፡ 18, 479 (0.71%)
• ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፡ 7, 136 (0.275%)
• የአሲምባ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፡ 774 (0.01%)

በክልሉ ምርጫ ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች መሳተፋቸው ይታወሳል።

በዚህ ምርጫ 190 መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት 625 እጩዎች ለመወዳደር ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ለመስጠት ተመዝግቦ ከ97 በመቶ በላይ ሕዝብ ድምጽ መስጠቱን የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመልክቷል።

በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በትግራይ በተናጠል የሚካሄደው ምርጫ ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።

ቢቢሲ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top