Connect with us

የካባ ፖለቲካ ትርፍ በጭብጨባ ማግስት ቆዳ የሚገፍ ሀሜት

የካባ ፖለቲካ ትርፍ በጭብጨባ ማግስት ቆዳ የሚገፍ ሀሜት፤

ነፃ ሃሳብ

የካባ ፖለቲካ ትርፍ በጭብጨባ ማግስት ቆዳ የሚገፍ ሀሜት

የካባ ፖለቲካ ትርፍ በጭብጨባ ማግስት ቆዳ የሚገፍ ሀሜት፤
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
የካባ ፖለቲካ ክፉ ድራማ ነው፡፡ ሐቀኞች በአግባቡ ስራቸውን እንዳይሰሩ ወደ ህዝብ አጀንዳ እንዳያተኩሩና ለውጥ እንዳያመጡ እንቅፋት ሲሆን አይተናል፡፡ ካባ አልብሶ ማማት አዲሱ የፖለቲካችን ባህል ሆኗል፡፡ ካባ አልብሶ ማቅ ለማልበስ የሚጣደፈው አስመሳይና አድር ባይ አጃቢ ከአጠገብ ለመበተንም የሚቅድመው የለም፡፡

ታከለ ኡማ ላይ ድራማ ሲሰራ የኖረው የጭብጨባ አጀብ ወደ ወይዘሮ አዳነች አበቤም ፊቱን አዙሯል፡፡ ሴትየዋ ጎበዝና አልፎ አሳቢ ቢሆኑም የወንበዴው ዘዴ ብዙ ሰው ጠልፎ ለማለፍ ስልቱ ብዙ ነውና ያሰጋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች አበቤ ካባ ተሸለሙ የሚለው ዜና ወርቀ ዘቦ ካባ በሚለው ቃል ሲሞካሽ ነገ የሚሆነውን ማሰብ ነው፡፡ ኢንጅነር ታከለን ወርቅ ያበሰው ቡድን ቆዳቸው በሀሜት ሲገፈፍ መረጃ አቀባይ ነኝ ብሎ ለመመጻደቅ የቀደመው አልነበረም፡፡

አዲስ አበባ ብዙ ችግሮች አሏት፤ ለማመስገን ከዛሬ ይልቅ ነገ ጥሩ ነው፡፡ ጥሩ የሰራ ሰው ዘመን ቆጥሮ የሚያመሰግነው ለመሆኑ ለሀገራችን ሰው የእኛኑ ጠባይ ማርዳት ለቀባሪ መንገር ነው፡፡ አሁንም ሆታ፤ ጫጫታ፤ ቲፎዞና ጭብጨባ ከተማ አይቀይርም፡፡
ከንቲባዋ የሚያጨበጭቡላቸውን እጆች ለስራ እንዲቆሽሹ መጋበዝ አለባቸው፡፡ አጠገባቸው የሚፈጠር ግርግር እንቅፋት ከመሆንና የስራ ጊዜያቸውን ከመሻማት ባለፈ የህዝብ ልብ የሚያስገኝ አቋራጭ አይደለም፡፡

አዲስ አበባ ብዙ ችግሮች አሉባት፡፡ የከንቲባው ካባ የነዋሪዋ ስኬታማ ህይወት ነው፡፡ አዲስ አበቤ ቤት አልባ ሆኖ በኑሮ ውድነት አበሳውን እያየ መብራትና ውሃ የገነት ያህል ናፍቀው ስራ አጥነት ቁጥሩ ገዝፎ ነገ ያለ ጨረታ ስራ ባገኝ በሚል ድራማ የሚሰራውን ሰው ማድመጥ ውጤቱ ምስጋና መቀበል ሳይሆን ከከተማው ህዝብ ልብ መራቅ ነው፡፡

የከተማዋ ጣጣ መብዛቱን ያሰበ የከንቲባ ወዳጅ ለለውጥ ሆ ብሎ ከጎናቸው በመቆም ለአዲስ አበባ እድገት ይደክማል እንጂ ካባ ጠልፎ ከንቲባ አይጠልፍም፡፡ የካባ ፖለቲካ እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ የተተቸ ብዙ የተገመተ ብዙ ያስተዛዘበ ቢሆንም ከለማ መገርሳ የጀመረው የካባ ማልበስ ድራማ ታከለ ኡማን አድርሶ አዲሷ ከንቲባ ጋር ሲመጣ እንደ ነዋሪ ለምን ማለት አይከፋም? ካባ ግን ለምን?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top