Connect with us

ሰው እንዴት በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ ይሆናል?

ሰው እንዴት በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ ይሆናል?
Photo: Facebook

ነፃ ሃሳብ

ሰው እንዴት በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ ይሆናል?

ሰው እንዴት በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ ይሆናል?
(ሙሼ ሰሙ)

ሰው ጦር ሳይሰብቅ፣ ሰራዊት ሳያዘመት እንዴት በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ ይሆናል። በገሃድም ሆነ በስውር ጦር ሰባቂዎች፣ ልዩ ጥበቃ በሚያገኙበት፣ በመንግስት ተሽከርካሪና ቤት በሚንደላቀቁበት ሀገር የልደቱ ጉዳይ “የፍትሕ ስርዓቱ” ተፋራጅ ሳይሆን በገዛ ሀገሩ የስርዓቱ ምርኮኛ ሆኖ ይሰማኛል።

በእርግጥ ልደቱ የሚታገለው ስርዓት ፍትሕን እንደማይሰጠው ቀድሞ ስለገባው ሲጮኽ ከርሟል። ይህም ሆኖ ግን፤ እንደ ዜጋ ስርዓቱ ፍትሕን ሊሰጠው ባይችል እንኳን፣ ሀገሬ ኢትዮጵያ የሞራል ሰው ድሃ ስላልሆነች ፍትሕ ሚኒስትሯ፣ ሰላም ሚኒስትሯ፣ አቃቤ ሕጉን፣ የኦሮሚያ ፍትሕና ቢሮን ጨምሮ ሌሎች ቱባ ሹመኞች “በውስጥ መስመርም” ቢሆን “እንግልቱ ይብቃ” በማለት በልደቱ ላይ የሚፈጸመው መሰረተ ቢስ ክስና ማንገላታት እንዲቆም ጣልቃ ይገባሉ ብዬ ነበር። አልሆነም!! ልደቱ በገዛ ሀገሩ ምርኮኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ፍትሕንም፣ ርትዕንም፣ ሰብአዊነትንም ተነፍጓል።

ብዙ ግፍ አይተናል፣ ብዙ ግፍ ሰምተናል፣ ዜጋውን ያለበቂና አስተማማኝ ምክንያት አግቶ/አስሮ፣ ለሳምንታት ያለ መረጃም ሆነ ማስረጃ ሲያመላልስ ከርሞ፣ ሁሉም መንገድ ወደታቀደለት አልወስድ በማለቱ የክስ መዝገብ ከተዘጋ በኃላ፣ ከሳሽ ሌላ ክስ እስኪፈጥርልህ ድረስ እስር ቤት ጠብቃቸው ማለት ግን፣ መቼስ በፍትሕ ስርአቱ ላይ የተፈጸመ የክፍለ ዘመኑ ፌዝ ይመስለኛል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top