Connect with us

መጀመሪያ ራሱን፤ አሁን ሀገር እያስሮጠ ያለው ኃይለኛው ኃይሌ

መጀመሪያ ራሱን፤ አሁን ሀገር እያስሮጠ ያለው ኃይለኛው ኃይሌ

ኢኮኖሚ

መጀመሪያ ራሱን፤ አሁን ሀገር እያስሮጠ ያለው ኃይለኛው ኃይሌ

መጀመሪያ ራሱን፤ አሁን ሀገር እያስሮጠ ያለው ኃይለኛው ኃይሌ።

አዳማ ኃይሌ ሪዞርት ተገኘሁ፡፡
**
(ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ)
አዳማ ነኝ፡፡ ኃይለኛው ኃይሌ ዛሬም ድል ያደርጋል፡፡ እዚህ ወንድም ወንድሙን ሲጥል እሱ ለሀገር ልጅ የእለት እንጀራ ቢበላ ብሎ ሞሰብ ይዘረጋል፡፡ አዲሱን ሞሰቡን ልመለከት መጣሁ፡፡ ኃይሌ ሪዞርት በአንዱ ሪስቶራንት መስተናገድ ከ1500 ዜጋ ጋር ገበታ መቅረብ።

ሻለቃው ዝም ብሎ ሰው አይደለም በሆቴልና ሪዞርት ዘርፍ እስከአሁን 1500 ዜጎችን ለስራ አብቅቷል። ቤተሰባቸውን ስንቆጥር ድምሩን ማስላት ነው።

 

አስቀድሞ ሮጠ፤ ራሱን ይዞ ሮጠ፡፡ አሸነፈ፤ እሱ ሲያሸንፍ ሀገር ተሸለመች፡፡ ስሙ የሀገር ስም ሆነ፤ ኢትዮጵያ አባቷ ኃይሌ መሰለ፤ በኃይሌ ስም ተጠራች፡፡ ደግሞ ልጇ ሆነ፤ ኃይሌ ኢትዮጵያ የሚለው ለዓለም እንግዳ ያልሆነ ስም ሆኖ ታተመ፡፡

 

አያርፍም፤ አይደክምም፤ ሜዲያሊያውን አውልቆ ያጠለቀላት ሀገር እያንዳንዱ ዜጋ ህይወቱ እንዲቀየር የሚመኝላት ለፍቶ አዳሪ ሆነ፡፡

ተመስጌን ብሎ ከመቀመጥ ተመስጌን የሚል ዜጋ ለመፍጠር ያለ እረፍት ተጋ፤ ከበቀለ ሞላ ቀጥሎ ሀገርን በሆቴል ኢንዱስትሪ ለማስጌጥ እንደ ወርቅ ጥሪቱ በእሳት እየተቃጠለ ተፈትኖ ባለፈ ሀገር የመቀየር ፍቅር ድልን ተቀናጀ፤ ያ አንድ ድል ዛሬ ተበስሯል፡፡

አዳማ ያመጣኝ ይህ ሰው በአዳማ የገነባውን አዲስ ሆቴል ሲከፍት ብስራቱን ልመለከት ነው፡፡ የአዳማው ሆቴል ሰባተኛው ነው።
ለ300 ዜጋ የሥራ እድል ፈጥሯል።

106 የመኝታ ክፍሎች አሉት። ባለ ሁለት ዘመናዊ የመመገቢያ አዳራሽ። ፈጣን ኢንተርኔት ስቲም ሳውናና ማሳጅ። ደረጃውን የጠበቀ መዋኛ የልጆች መጫወቻ መአከል። ሰባት እስከ ሺህ ሰው የሚይዙ የስብሰባ አዳራሾች። በቂ የመኪና ማቆሚያ ደከመኝ። ብቻ ቅንጡ ነው። ግማሽ ቢሊዮን ብር እንዳወጣበት ጀግናው ገልጿል።

ኃይሌን መንፈስ ለመላው ኢትዮጵያዊ እንዲሰጠው ተመኘሁ፡፡ ሀገሬ የኔ ናት የሚለውን መንፈስ፤ ሀገሬን አልተውም የሚያስብልን፤ ለሀገሬ እኔ አለኋት ብሎ የሚያስቆጭን መንፈስ፤ የመንጠቅ ሳይሆን የመስጠትን መንፈስ፤ ወጣት ሜዳ የመበተንን ሳይሆን ወጣት የመሰብሰብን መንፈስ፤ የዚያ ውጤት ይህ ልማት ነው፡፡

አዳማ ተጨማሪ ሆቴል አገኘች ብዬ የማቀለው ዜና አይደለም፡፡ የአዳማ ልጆች አዲስ የስራ እድል ተፈጠረላችው የሚለው እውነት ቢሆንም ትርጉሙ ግን ይልቃል፡፡
ሰውዬው የላቀ ኢትዮጵያዊ ነውና፤

ኃይሌ ሪዞርት ሶዶ አዲስ አበባና ኮንሶ ግንባታ ላይ ነው። ደብረ ብርሃንና ጎርጎራ ቀጣዮቹ መዳረሻዎች ናቸው።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top