Connect with us

ዉኃ አራት ሰዉ በላ፣ ሺዎችን አፈናቀለ

ዉኃ አራት ሰዉ በላ፣ ሺዎችን አፈናቀለ
Photo: Social Media

ዜና

ዉኃ አራት ሰዉ በላ፣ ሺዎችን አፈናቀለ

የኦሞ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ዉኃ ከከባቸዉ መንደሮች ለማምለጥ የሞከሩ አራት የደቡብ ክልል፣ የዳሰነች ወረዳ ነዋሪዎች ሞቱ።

የአካባቢዉ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት አራቱ ሰዎች በዉኃ የተበሉት ዉኃ ከከበባት ቶል-ታሌ ቀበሌ ወደ ደረቅ መሬት በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ጀልባቸዉ ተገልብጣ ነዉ።

ከሟቾቹ ሁለቱ እናት እና ልጅ ሁለቱ ደግሞ አዛዉንቶች ነበሩ። በውኃ ተከበው የነበሩ ሌሎች 200 ነዋሪዎች ግን ከክልሉ በተላኩ ጀልባዎች ርዳታ ሙሉ በሙሉ ወደ ደረቅ አካባቢ መሻገራቸዉን የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ መላኩ ለማ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

የኦሞ ወንዝ ሙላት ከዳሳች ወረዳ 40 ቀበሌዎች መካከል 28ቱን አጥለቅልቋል። ከ15 ሺሕ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል።

የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋን ግዛዉ ወጋየሁ እንደዘገበዉ የዉኃ ሙላቱ ከ30 ዓመት ወዲሕ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።

ከዳሰነች ወረዳ በተጨማሪ በደቡብ ክልል ካለፈው ሰኔ ጀምሮ በጎርፍና በመሬት ናዳ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ28 ሺህ መብለጡን የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የደቡብ ክልል መስተዳድር ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በመተባበር ለተፈናቃዮች ምግብና መጠለያ እየረዳ መሆኑን ኮሚሽነር ጋንታ ጋሩማ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ። #DW

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top